You are currently viewing የቫይታሚን ዲ እጥረት እና ኮቪድ-19 ‼️

የቫይታሚን ዲ እጥረት እና ኮቪድ-19 ‼️

September 5 2020

የ ቫይታሚን ዲ እጥረት ለኮቪድ-19 በሽታ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጋልጥ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

👉 “ጃማ ኔትወርክ” በተባለ የምርምር መጽሔት የወጣው ግኝት እንደሚያመለክተው የ ቫይታሚን ዲ ንጥረ ነገርን በበቂ ሁኔታ የማያገኙ ሰዎች በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የመያዛቸው ዕድል ከ77 በመቶ በላይ ነው፡፡

👉 ዩፒአይ የምርምር ጽሑፉን ጠቅሶ እንደዘገበው ከ5 መቶ ናሙናዎች ውስጥ የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው ሰዎች 22 በመቶ በቫይረሱ ሲያዙ እጥረቱ ካልገጠማቸው 12 በመቶዎቹ ብቻ ተጠቂ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

👉 የጥናት ቡድኑ ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ዴቪድ ሜልትዘር እንዳሉት የቫይታሚን ዲ ንጥረ ነገር በሽታ የመከላከል አቅማችንን ከማጠናከር ባሻገር በኮቪድ-19 ስንጠቃ የሚያጋጥመንን የሰውነት መዳከም ያስወግዳል ብለዋል፡፡

 

#EBS

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply