You are currently viewing በኢትዮጵያ ​​በኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) ተይዘው ወደ ፅኑ ህክምና የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው‼️

በኢትዮጵያ ​​በኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) ተይዘው ወደ ፅኑ ህክምና የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው‼️

 

August 24 2020

የሚሊኒየም የኮቪድ-19 ህክምና ማእከል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ማእከሉ ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች ብቻ እየተቀበለ ነው።

በማእከሉ የሚገኘው የኦክስጅን ህክምና መስጫ ክፍልም በህሙማኑ ቁጥር መጨመር ምክንያት እየሞላ መሆኑን የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ በየቀኑ እስከ 20 የሚደርሱ በፀና የታመሙ ታካሚዎች ወደ ማእከሉ እየገቡ ነው ብለዋል፡፡

የህሙማን ቁጥር በዚህ ከቀጠለም ማእከሉ ህሙማንን የማስተናገድ አቅሙ ፈተና ውስጥ እንደሚገባ ጠቅሰው ለዚህም ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት መሆኑን አውስተዋል።

በማእከሉ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋቸው 217 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን 44ቱ ሰዎች በፀና የታመሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዶክተር ውለታው እንደሚሉት አብዛኞቹ የኦክስጅን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን በየቀኑ ወደ ማእከሉ የሚገቡ እና በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥርም ጨምሯል።

ይህም ሆኖ ከፍተኛ የሆነ የማሽን እጥረት መኖር፣ለፅኑ ህከምና የሚሆን መድሀኒት እጥረት እና ሌሎች ግብአቶች አለመሟላት በታማሚዎች መብዛት ምክንያት እጥረት እየታየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንም ተጓዳኝ ህመም የሌለባቸው እና በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎችም ህይወታቸው እያለፈ እና በፀና እየታመሙ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ማእከሉ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከ 2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑትን ያከመ ሲሆን 22 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት በማእከሉ ህይወታቸው ማለፉን አንስተዋል።

በማእከሉ ከአራት በላይ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ እንደተገኘባቸው በመጥቀስም ህብረተሰቡ መዘናጋቱን እንዲያቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) የተገኘባቸው ሰዎች ሰዎች ቁጥር ከ40 ሺህ በላይ ሲደርስ ከ600 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

 

#FBC

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply