You are currently viewing የማይግሬን እራስ ምታትን መረዳት‼️

የማይግሬን እራስ ምታትን መረዳት‼️

June 25 2021, Doctors Online Ethiopia

የጥያቄዎቻችሁ መልስ

✔️ ማይግሬን በተደጋጋሚ የሚከሰት በአይነቱ  ውስብስብ የራስ ምታት ህመም ነው:: በሽታው የሚከሰተው በተለያዩ ምክንያቶች በሚመጣ የነርቭ ስርአት መዛባት ነው::

✔️ የማይግሬን የራስ ህመም አብዛኛውን ጊዜ ከፍሎ እራስን በአንድጎን የሚያም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ እራስ ምታቱ ከመከሰቱ በፊት ከእይታ ወይም ከስሜት ህዋሳት ጋር የተያያዙ ጠቋሚ የሆኑ ምልክቶች (Aura) ሲኖሩት እነዚህ ምልክቶች በራስ ምታቱ ወቅት ወይም ከራስ ምታቱ በኋላ ሉከሰቱም ይችላሉ::

✔️80 በመቶ ማይግሬን በሴቶች ዘንድ የሚታይ ቢሆንም ወንዶች ላይ በሽታውን ማየት ያልተለመደ አይደለም:: በተጨማሪም የማይግሬን እራስምታት በዘር መተላለፍ የሚችል የበሽታ አይነት ነው፡፡

 

የተለመዱ የማይግሬን ምልክቶች

👉የሚወጋ (Throbing ) አልያም ትርትር የሚል (Pulsatile) በእንቅስቃሴ ጊዜ ወይም ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ መጠኑ የሚጨምር ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የራስ ህመም

👉 ውስን ቦታ ላይ ያለ ብዙ ጊዜ በአንድ ጎን የሚከሰት በአይን እና በግንባር አካባቢ ያለ ህመም

👉 ህመሙ ቀስ በቀስ ከ1-2 ሰአት ውስጥ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን እራስ ምታቱ ከ4 ሰአት እስከ 3 ቀን ሊቆይ ይችላል::

👉 ማቅለሽለሽ ከመቶ ታማሚዎች መሀል ሰማኒያዎቹ ላይ ይኖራል::

👉 ማስታወክ ከመቶ ታማሚዎች መሀል ሀምሳዎቹ ላይ ይታያል::

👉 በብርሃን እና በድምጽ መረበሽ (Sensitivity to light and sound)

አንድ ሰው ማይግሬን አለበት እንዲባል ከሚከተሉት ምልክቶች ቢያንስ 2 ሊኖረው ይገባል::

1. በአንድ ጎን የሚከሰት እራስ ምታት

2. ትር ትር የሚል እራስ ምታት

3. ህመሙ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ

4. በእንቅስቃሴ የሚባባስ ወይም ህመምተኛውን ከመደበኛ እንቅስቃሴ ያስተጓጎለ::

በተጨማሪም ታማሚው በህመሙ ወቅት ወይ ወደላይ ማለት/ማስታወክ አልያም በድምፅ/በብርሃን መረበሽ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን እነዚህ ምልክቶች በሌላ በሽታ የመጡ መሆን የለባቸውም::

 

የማይግሬን ራስ ምታት እንዴት ይታከማል?

✍️ የዚህ ህመም ተጠቂ ህመሙን የሚቀስቅስበት ምን ሁኔታ ወይም ነገር እንደሆነ ለይቶ በማወቅ ቀስቃሹን ነገር ወይም ሁኔታ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡

👉 የማይግሬንን የራስምታትን የሚቀሰቅሱ የሚከተሉትን ይመስላሉ የሚከተሉት ናቸው::

1. ጭንቀት

2. የእንቅልፍ መዛባት

3. ፆም

4. አብረቅራቂ ነገሮችን መመልከት

5. አንዳንድ ሽታዎች

6. የሲጋራ ጭስ

7. አልኮል መውሰድ- በዋነኝነት ወይን እና ቢራ

8. ካፌን ያላቸው ምግቦች እንደቸኮሌት፣ ቡና ወዘተ…

👉 ህመሙን የሚቀሰቅሱብንን ነገሮች አውቆ ማስወገድ ህመሙ አስቀድሞ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

✍️ መጠነኛ እና መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የህመሙን መጠን ያወርደዋል::

✍️ ዮጋ እና አንዳንድ ሌሎች ዘና የማያ ዘዴዎች(Relaxation Techniques)

✍️ በቂ ውሃ መጠጣት – አንድ ጥናት እንዳሳየው በቀን ውስጥ የሚጠጡትን የውሃ መጠን በ1.5 ሊትር መጨመር ማይግሬን የእራስ ምታቱን መጠን እና ድግግሞሽ ይቀንሰዋል::

✍️ የማይግሬን የራስምታትን ለማከም፣ እንደ የራስምታቱ ክብደት የተለያዩ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ቀለል ላለ የ የማይግሬን ራስምታት፣ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከላይባሉት መንገዶች በሽታውን መቆጣጠር ካልተቻለ ወደሀኪም ጋር በመሄድ መታየት ያስፈልጋል::

Leave a Reply