You are currently viewing ዶክተሩ ቀዶ ሕክምና እያካሄደ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል በዙም መቅረቡ ተነገረ‼️

ዶክተሩ ቀዶ ሕክምና እያካሄደ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል በዙም መቅረቡ ተነገረ‼️

March 1 2021, News

በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት አንድ ዶክተር ለታማሚው የቀዶ ሕክምና እያካሄደ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ዙም ላይ መግባቱ ተነገረ።

ዶክተር ስኮት ግሪን ለቀዶ ሕክምናው የሚረዱት አልባሳትን ለብሶ እና በቀዶ ሕክምና ክፍል ውስጥ ሆኖ ነበር የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል በኢንተርኔት አማካኝነት በቪዲዮ የቀረበው።

የዕለቱ ዳኛ ዶክተር ግሪን ለፍርድ ሂደቱ ዝግጁ መሆኑን ሲጠይቁት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመከታተል ዝግጁ መሆኑንና ጠቅሶ፤ “አጠገቤ ሌላ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ይገኛል’ ሲል አስረድቷል።
ዳኛው ግን ይህ አካሄድ ተገቢ አይደለም በማለት የፍርድ ሂደቱ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ወስነዋል።

የካሊፎርኒያ የሜዲካል ቦርድ በበኩሉ ጉዳዩን እንደሚከታተለውና የሕክምና ባለሙያዎች ስራቸውን ሲሰሩ የተቀመጡ አካሄዶችን በአግባቡ መከተል እንዳለባቸው አሳስቧል።

በአሜሪካ ሕግ መሰረት የትራፊክ ጥፋቶችን የፈጸሙ ሰዎች የፍርድ ሂደት ለህዝብ ይፋ መሆን ያለባቸው ሲሆን፤ ይህ የፍርድ ሂደትም በዩትዩብ አመካይነት በቀጥታ ሲተላለፍ ነበር ተብሏል። ዶክተሩም በዚህ መልኩ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ፈቃደኛ መሆኑ ሲጠየቅ ”ምንም ችግር የለውም፤ መቀጠል እንችላለን። አብሮኝ ደግሞ ሌላ ባለሙያ አለ” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በአሜሪካ ሕግ መሰረት የትራፊክ ጥፋቶችን የፈጸሙ ሰዎች የፍርድ ሂደት ለህዝብ ይፋ መሆን ያለባቸው ሲሆን፤ ይህ የፍርድ ሂደትም በዩትዩብ አመካይነት በቀጥታ ሲተላለፍ ነበር ተብሏል። ዶክተሩም በዚህ መልኩ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ፈቃደኛ መሆኑ ሲጠየቅ ”ምንም ችግር የለውም፤ መቀጠል እንችላለን። አብሮኝ ደግሞ ሌላ ባለሙያ አለ” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የዕለቱ ዳኛ ጌሪ ሊንክ የፍርድ ሂደቱን ለመምራት ሲቀመጡም ዶክተር ግሪን የቀዶ ሕክምና ስራውን አላቆመም ነበር።

ዳኛውም ”ካልተሳሳትኩ በአሁኑ ሰዓት የቀዶ ሕክምና እያካሄድክ ነው። ትክክል ነኝ?” በማለት ጠይቀዋል። ዶክተር ግሪንም “አዎ እውነት ነው፤ የፍርድ ሂደቱንም መቀጠል እችላለሁ” ብሏል።

ዳኛ ጌሪ ሊንክ ግን በዚህ አካሄድ ደስተኛ አለመሆናቸውንና ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ማሳያዝ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ”ይህ ሊሆን አይችልም፤ ይህ ተገቢ አይደለም። በቀዶ ሕክምና ክፍል ውስጥ ስራህን እየሰራህ የፍርድ ሂደቱን ልትከታተል አትችልም። ተገቢም ትክክልም አይደለም” ብለዋል።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ዶክተር ግሪን ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቆ ነበር። ኤንቢሲ ኒውስ ከዶክተሩ አገኘሁት ባለው አስተያየት ”መረጃው ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም፤ ሌላ የምለው ነገር የለም። አመሰግናለሁ።” የሚል ምላሽ መስጠቱን ዘግቧል።

 

#BBC

Leave a Reply