October 29 2020
ለመሆኑ ማድያት ምንድነው?
ማድያት (melasma) ማለት በፀሐይ የጠየመ ወይም የጠቆረ የቆዳ ቀለም ቅየራ ማለት ነው። ማድያት ለፀሐይ በተጋለጡ የሰውነት ክፍሎች ላይ በብዛት ፊት ላይ ይከሰታል። በዋናነትም ሴቶችን በተለይ ጥቁር/ጠይም የቆዳ ቀለም ያላቸውንና ለፀሐይ ጨረር(UV radiation) የተጋለጡትን ያጠቃል።
መንስኤዎቹ ፦ በብዛት መንስኤው አይታወቅም
እርግዝና
– በአፍ የሚዋጡ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶች
– ለፀሐይ መጋለጥ
– በቤተሰብ ማድያት ካለ
– የመዋቢያ ቅባቶች
– የሚጥል በሽታ መድኃኒቶች
– የእንቅርት በሽታ
– የኩላሊት ዕጢ በሽታ(addisons disease)
ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
ጠቆር ያለ፡ ቅርፅ አልባና ከጤነኛው ቆዳ በደንብ መለየት የሚችል ከትንሽ እስከ ትልቅ መጠን ያለው የቆዳ መዝጎርጎር። በዋናነት ሦሥት አይነት የማድያት ስርጭት አለ
1. Centrofacial፦ ጉንጭን፣ ግንባርን፣ የላይኛውን ከንፈር፣ አፍንጫና አገጭን ያጠቃለለ ሲሆን
2. Malar፦ ጉንጭንና አፍንጫን ሲያጠቃልል
3. Mandibular፦ የታችኛውን ግንጭል ያጠቃለለ ከሆነ
ለማድያት ምን ምርመራ ይታዘዛል?
– አካላዊ ምርመራ
– የጨረር ምርመራ(wood’s lamp)
ህክምናው ምንድን ነው?
ማድያትን ለመታከም ወደህክምና ተቋማት ሲሄዱ ሊደረግሎ ከሚችሉ ነገሮች መካከል በጥቂቱ:-
- ማድያት በረጅም ጊዜ የሚመጣና በዘላቂነት የመቆየት ባህሪ ስላለው በቶሎ ለማከም አስቸጋሪ ነው። በዋናነት ግን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የሚቀቡ መድኃኒቶችን እና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ(ከተገኘ ለዚህ ተብለው የተሰሩ፣ አለበለዚያ ማንኛውንም ጨርቅ እና ባርኔጣ/ኮፍያ መጠቀም ይቻላል) መጠቀም አስፈላጊ ነው።
ምናልባት ግን ማድያቱ በእርግዝና የመጣ ከሆነ ልጅ ከተወለደ እስከ አንድ አመት ባለው ጊዜ ሊጠፋ ይችላል። - የሚያነጡ መድኃኒቶች መጠቀም(hydroquinone, azelaic acid, tretinoin…)
- ቆዳን የሚልጡ ኬሚካሎች(chemical peels)፦ ይኸ በቆዳ ስፔሻሊስት ሐኪም ምክር ብቻ የሚከናወን ነው
- የጨረር ህክምና(laser theraphy)
- የፊት ሜካፕ(cosmotic camouflage) በመጠቀም ማድያቱ እንዳይታይ ማድረግም ይቻላል::
By Tena Mereja
Subscribe to Our YouTube Channel For Interesting Health Related Topics