You are currently viewing ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው?

ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው?

 በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም

ከአንድ እስከ ሶስት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ አይጨነቁ። ግን ምግብ በደንብ የሚበላ ልጅ ምግብ በተደጋጋሚ ከቀነሰ ያን ጊዜ የልጅውዎን ሀኪም ያማክሩ።

አንዳንዴ ምግብ መብላት ለልጆች እንደ ስራ ከባድ ይሆንባቸዋል። ይህን እንዴት እንደምናስተካክለው ቀጥሎ ይመልከቱ።
1. የህጻናትን የምግብ ፍላጎት ያክብሩ፥ የምግቡን አይነት ሳይፈልግ ምግብ እይስጡ::
ህፃናት አዲስ ምግብ እንዲለምዱ እድል ይስጡ። ሳይቀምሱ አልወድም ወይም ያስጠላል ስለሚሉ መጀመሪያ ጣእሙን እና ቀለሙን እያደነቁ ይቅመሱላቸው ከዚያ እንዲሞክሩ ይጋብዙ።
አስገድደው ውይም ደልለው ለመመገብ አይሞክሩ ምክንያቱም በምግብ ሰአት ሁልጊዜ እንዳይጨነቁ።
ልጅዎ የማይወደውን ምግብ በራበው ሰዓት ለመስጠት ይሞክሩ። ምግቦችን በተለያየ ቀልም እና ጣእም ያለማምዱ።
2. የተለመደ የምግብ ሰዓት ያስለምዱ – ሁልጊዜ በተመሳሳይ ሰአት ይመግቡ።
ምግብ አልበላም ሲሉ ወተት ወይም ጭማቂ፣ ጣፋጭ ምግብ የሚሰጡ ከሆነ ይከልክሉ።
3. አዳዲስ ምግቦችን ለማስለመድ ትእግስተኛ ይሁኑ
ህፃናት አዲስ ምግብ ነክተው አሽትተው በምላስ ቀምሰው ተፍተው ነው የሚለምዱት። ግን ደጋግመው እንዲሞክሩ እድል ይስጧቸው ይሳካል።የምግቡን ቀለም፣ቅርፅ ሽታውን እየነገሩ እንዲወዱት ያድርጉ። አዳዲስ ምግቦችን ከለመዱት ጋር በማቀላቀል ይስጡ።
4. እንደ ምግብ ቤት የሚፈልጉትን ምግብ ብቻ እንዲያዙ እድል አይስጡ።
አንድን ምግብ እምቢ ሲሉ ወዲያው ተለዋጭ ምግብ ለመስራት አይቸኩሉ። ቢመገቡም ባይመገቡም የቀረበ መአድ እስኪነሳ ከገበታ ላይ እንዳይነሱ ያድርጉ። ይህም የመአድ ጊዜን ማክበር እንዲማሩ ያግዛል።
5. ምግብ ሲሰሩ የምግቦች ቅርፅ ልጅ ሳቢ እና አመራማሪ እንዲሆን አድርጉ። አንዳንዴ የቁርሱን ምግብ በራት ሰዓት የምሳውን ለቁርስ ሰዓት አድርገው ምግብን እንዲወዱ ማስደመም ይችላሉ።
6. አትክልት ስንገዛ ልጆች አብረውን ካሉ የሚፈልጉትን አትክልት እንዲመርጡ እድል ይስጡ።
7. ቤተሰቡ የሚመገበውን ምግብ በማፍራረቅ ለህፃናት አርአያ ይሁኑ።
8. ምግቦችን የፈጠራ ችሎታን ተጠቅሞ መስራት ልጆች በቀላሉ እያድነቁ እንዲበሉ ያደርጋል። የተፈጨ ብሮኮሊ ከሩዝ ወይም ከፓስታ ጋር ወይም የተፈጨ ጎመን ወይም ካሮት ከሾርባ …ወዘተ
9. በምግብ ሰአት ሀሳብ የሚሰርቁ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችን ያጥፉ።
10. እባክዎ ይህን ከበላህ/ሽ ይህን እሰጥሀለሁ ብለው ምግቦችን አያበላልጡ። ከምግብ በኋላ ፍራፍሬ እንጂ ጣፋጭ አያስለምዱ።
11. የምግብ ሰዓትን የምግብ እና አመጋገብ መማሪያ ማድርግ እና ልጆች ስለሚመገቡት ምግብ አመጋገብ ዘዴ ፣ ምንነት እና ጥቅም እንዲያዉቁ ያድርጉ።
12. በምግብ ሰአት የሚያወሩት ገንቢ ሀሳብ እና አስደሳች ከሆነ ይህንን ጊዜ ቤተሰቡ ይናፍቀዋል።
13. ምግብ እኛ እናቅርብላቸው ወይስ ራሳቸውን ያስተናግዱ የሚለውን በየወቅቱ መለዋውጥ
14. ልጆች ምግብ እንዲሰሩ ወይም ሲሰራ እንዲያዪ እድል ይስጡ። ይህም ምግብን እየወደዱ እንዲመገቡ ያግዛል።
ይህ ሀሳብ ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ።
ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ "ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው"
ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ

Leave a Reply