You are currently viewing የማኅበረሰብ በሽታ የመከላከል አቅምን እንደ ኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴ አድርጎ ማቅረብ ኢ-ሞራላዊ ነው፡- የዓለም ጤና ድርጅት

የማኅበረሰብ በሽታ የመከላከል አቅምን እንደ ኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴ አድርጎ ማቅረብ ኢ-ሞራላዊ ነው፡- የዓለም ጤና ድርጅት

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

October 13 2020

የማኅበረሰብ በሽታ የመከላከል አቅምን /herd immunity/ን እንደ ኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴ አድርጎ ማቅረብ ኢ-ሞራላዊ እና የሙያ ሥነ-ምግባርን ያልተከተለ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በትላንትናው ዕለት በሰጡት የኮቪድ-19 ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ እንዳሉት፣ “የማኅበረሰብ የበሽታ መከላከል አቅምን ለማጎልበት ኮቪድ-19 ኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲሠራጭ መፍቀድ አለብን” በሚል የሚቀርቡ ሀሳቦች በሳይንሱም ሆነ ከሥነ-ምግባር አኳያ አግባብ አይደለም።

የማኅበረሰብ በሽታን የመከላከል አቅም ከክትባት ጋር ተያያዞ የሚነሳ ፅንሰ-ሐሳብ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አንድ ሕዝብ ከቫይረሱ ራሱን መከላከል የሚችለው ክትባትን በበቂ ሁኔታ ማዳረስ ሲቻል ነው ብለዋል።

በቂ የሚባለው የክትባት ደረጃም እንደየቫይረሱ ዓይነት እንደሚለያይ ነው የገለጹት።
የኩፍኝ በሽታን እንደ ምሳሌ በማንሳትም፣ ከአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ 95 በመቶ ክትባት ቢያገኝ ቀሪው 5 በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም እንደሚያጎለብት አስረድተዋል።

ለፖሊዮ ደግሞ በቂ የክትባት ደረጃ የሚባለው 80 በመቶ የማኅበረሰብ ክፍል ሲከተብ እንደሆነ ተናግረዋል።
“የማኅበረሰብ በሽታን የመከላከል አቅም ማጎልበት የሚቻለው ሰዎችን ከቫይረሱ በመከላከል እንጂ ለቫይረሱ እንዲጋለጡ በማድረግ አይደለም” ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ።

የማኅበረሰብ በሽታን የመከላከል አቅም ኮቪድ-19ን ለመሰለ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ይቅርና ለየትኛውም ዓይነት ወረርሽኝ እንደ ስልት ሲያገለግል በማኅበረሰብ ጤና ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ መሆኑንም ነው ዶ/ር ቴድሮስ የተናገሩት።

“በአግባቡ ላልተረዳነው ለዚህ አደገኛ ቫይረስ ሕዝቡን ማጋለጥ ሥነ-ምግባር የጎደለው እርምጃ ነው” ሲሉ መኮነናቸውን ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበዋል።

#EBC

Leave a Reply