You are currently viewing የሀኪሙ ገጠመኝ ፤ ጉዞ ወደ ገነት…

የሀኪሙ ገጠመኝ ፤ ጉዞ ወደ ገነት…

October 8 2020

ዶ/ር ሠኢድ መሐመድ (የአጥንት ስፔሻሊስት)

አንዱ ታካሚ ሠሞኑን የግራ እግሩ እና የቀኝ እጁ ላይ በደረሠበት የአጥንት ስብራት ምክንያት ሆስፒታል ተኝቶ ይታከማል። ይህንን ታካሚ ሊጠይቁ ወደተኛበት ክፍል የሚገቡ ሠዎች ግን ግለሠቡ ተሠባብሮ የተኛ ሳይሆን ለመዝናናት ባህር ዳርቻ ላይ ጋደም ያለ ይመስል ጣሪያው እስኪሠነጠቅ ከትትት ብለው ይስቃሉ። የሁኔታውን መደጋገም ያስተዋለ አንድ የሆስፒታሉ ሠራተኛ ታዲያ አንድም የገባ ሁሉ የሚስቅበትን ምክንያት ለማወቅ በመጓጓቱ እና ይህን ያህል ሳቅ ሆስፒታል ውስጥ ተገቢ አለመሆኑንም ለማስታወስ ፣ ጠያቂ አለመኖሩን ባረጋገጠበት ሠዓት ከታካሚው አንደበት ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክፍሉ ገባ። ሁኔታው ሲነገረው ግን እርሱም ሳቁን መቆጣጠር አልቻለም።

ታካሚው ታሪኩን ያስረዳል…

“የምኖረው አዲስ አበባ ውስጥ ፣ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው እና G+1 በሆነው የወላጅ አባቴ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። በቀደም፣ አንደኛው ፎቅ ላይ በሚገኘው መኝታ ቤቴ በተለመደው ሁኔታ ተኝቼ ሳለሁ፣ በህልሜ ከሞት በኋላ አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ከበርካታ ህዝብ ጋር እየተጋፋሁ ፊት ለፊታችን ከፍ ያለ ቦታ ላይ የቆመ አንድ መልዓክ የሚሠጠውን መግለጫ ለመከታተል ስታገል ተመለከትኩ። ትንሽ ራቅ ብሎ በርካታ “ካቻ ማሌ” አውቶብሶች ተኮልኩለዋል። መልዓኩ ስም ዝርዝር እንደሚጠራ እና ገነት ለመግባት የተወሰነላቸው ሠዎች በስተቀኝ በኩል ባሉት ባሶች፣ ገሃነም የተፈረደባቸው ደግሞ በስተግራ በኩል ባሉት ባሶች እንዲሳፈሩ ካሳሰበን በኋላ ስም ዝርዝሩን ማንበብ ቀጠለ። ብዙም ሳልጠብቅ የእኔ ስም ተጠራ እና ወደ ገነት እንድሄድ አበሠረኝ።

እጅግ እየተደሰትኩ ወደተነገረኝ አውቶብስ ገብቼ ተሳፈርኩ። አውቶብሱ የተወሰነ መንገድ ከወሰደን በኋላ ግን እየሄደ ያለበት መንገድ ወደ ገሃነም እንደሆነ አስተዋልኩ። ሹፌሩን ጠርቼ መንገድ እንደሳተ ብነግረውም ሊሠማኝ አልፈቀደም። እየጮህኩኝ ለተሳፋሪዎች ሁኔታውን ለማስረዳት ሞከርኩ። ሠሚ ግን አልነበረም። ምናልባት የማውቀው ሠው ካለ ብዬ ዘወር ዘወር እያልኩ ተሳፋሪውን ስመለከት፣ አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ማስክ አድርገው ስለነበረ ፊታቸውን ለመለየት ተቸገርኩ። ቀና ስል በፊት ለፊቱ መስታወት ከርቀት ገሃነም ታየኝ… እየደረስን መሆኑ ነው። ከኔ ሌላ ግን ሁሉም ተሳፋሪ ሁኔታው አልገረመውም። አውቶብስ ተሳስቼ መሆን አለበት! … በስህተት የተሳፈርኩት ወደ ገሃነም የሚሄደው ላይ መሆኑን አመንኩ። በቅፅበትም ለማምለጥ ወስኜ በስተግራዬ የሚገኘውን የአውቶብሱን መስኮት ባለ በሌለ ሃይሌ በመስበር እጄ እየደማ በመስኮት ዘለልኩ። …

Leave a Reply