You are currently viewing የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሰሐራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚ‼️

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሰሐራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚ‼️

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በረሐ በታች በሚገኙ አገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጎርጎሮሳዊው 2020 ዓ.ም. 40 ሚሊዮን ሰዎችን ወደ ከፋ ድሕነት ሊገፋ እንደሚችል የዓለም ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ዛሬ ይፋ ባደረገው ትንበያ መሠረት ከሰሐራ በርሐ በታች የሚገኙ አገራት ምጣኔ-ሐብት በ3.3 በመቶ ሊቀንስ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

በዓለም ባንክ ትንበያ መሰረት የአኅጉሩ ኤኮኖሚ በጎርጎሮሳዊው 2021 ዓ.ም አገግሞ በ2.1 በመቶ ሊያድግ ይችላል። ይኸ ባለፈው አመት ከነበረው 2.4 በመቶ ዕድገት ያነሰ ይሆናል።

ከደቡብ አፍሪካ በቀር ሌሎች ከሰሐራ በርሐ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ወረርሽኙ ካስከተለው የከፋ የጤና ቀውስ ያመለጡ ይመስላል። በመላው ዓለም በኮሮና ከተያዙ ሰዎች መካከል 3.4 በመቶው በዚሁ ቀጠና የሚገኙ ናቸው። በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸውን ካጡ ሰዎች 2.5 በመቶው ከሰሐራ በርሐ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ይኖሩ ነበር። የዓለም ባንክ ግን ወረርሽኙ የሚያስከትለው ዳፋ ሊከፋ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከሰሐራ በረሐ በታች የሚኖሩ ዜጎችን ሕይወት ከ13 አመታት በፊት ወደ ነበረበት ሊቀለብስ እንደሚችል ያስጠነቀቀው የዓለም ባንክ የ235 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርት ሊስተጓጎል እንደሚችል ጠቁሟል።
በዚህ አመት የኢኮኖሚ ዕድገት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ገቢራዊ በተደረጉ ክልከላዎች ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ይጠበቃል።

“በቱሪዝም ኢንዱስትሪ በሚፈጠር መናወጥ እና በእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና በደሴት አገሮች መቀዛቀዝ ይፈጠራል::( የዓለም ባንክ )

Leave a Reply