You are currently viewing መልካም የእይታ ቀን‼️

መልካም የእይታ ቀን‼️

October 8 2020

ዓለም አቀፉ “የእይታ ቀን” በመላው ዓለም እየተከበረ ነው::

ዓለም አቀፉ “የእይታ ቀን” የእይታ ችግር ላለባቸው እና ለአይነስውራን ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲሰጣቸው በማለም በየአመቱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥቅምት በገባ ሁለተኛው ሀሙስ የሚከበር ቀን ነው።

የዘንድሮው የእይታ ቀንም “ተስፋችን በእይታችን” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በዓለማችን አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች አስቀድሞ መከላከል በሚቻል የዓይን እይታ ችግር እንደሚጠቁ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
የአይን እይታ መቀነስ ችግር በእለት ተለት እንቅስቃሴ፣ ከማህበረሰብ ጋር ግንኙነት እንዲሁም የስራ እድል ላይ ዘርፈ ብዙ ችግር እያስከተለ ይገኛል።

የእይታ መቀነስ ችግር እና አይነስውርነት በስኳር በሽታ፣ ትራኮማ፣ ትራውማ፣ ግላኮማ እና ከእድሜ ጋር ተያያዥ በሞኑ ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የእይታ ችግር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተለይ እድሜያቸው ከ50 ዓመት መላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን አይነስውርነት ግን በማንኛውም እድሜ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል።

Leave a Reply