You are currently viewing የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ ይሰጣል ተባለ‼️

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ ይሰጣል ተባለ‼️

October 7 2020

የትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርት ለመጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ  እና  በትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ግብዕቶች ለማሟላት ስራዎችን  እየሰራ መሆኑን አስታወቋል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ  ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለሁሉም  የመንግስት እና የግል ትምህርት  ቤቶች  የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በነፃ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውም  አዲስ አበባ እና ሀዋሳን ማዕከል በማድረግ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮ እንደሚከፋፈሉ ዳይሬክተሯ አስታወቀዋል፡፡የአለም የጤና ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ  የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችም  ሀገር ውስጥ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግዢ የመፈፀም ስራ እየተከናወነ እና በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡ለተማሪዎች የሚከፋፈለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ  በተደጋጋሚ ታጥቦ ዳግም አግልግሎት መስጠት የሚችል  እንደሆነም ተነግሯል፡፡

Leave a Reply