You are currently viewing የሀኪሙ ገጠመኝ‼️  “ዶክተር አርግዣለሁ አልኩህ አርግዣለሁ!”

የሀኪሙ ገጠመኝ‼️ “ዶክተር አርግዣለሁ አልኩህ አርግዣለሁ!”

October 7 2020

ዶ/ር አብዮት ህላዊ (የፅንስ እና ማህፀን ስፔሻሊስት)

——————————————————

በምሠራበት የግል የህክምና ተቋም አስቂኝም አሳዛኝም የሆኑ የተለያዩ ክስተቶች ያጋጥሙኛል። ዛሬ ላጋራችሁ የወደድኩት ስለአንዲት የሃያ ስድስት ዓመት ዕድሜ ያላት ታካሚዬ ግርምት ያሳደረብኝን ገጠመኝ ነው።

እንደተለመደው በስራ ቢዚ በሆንኩበት ሠአት ፊቷ ላይ ድንጋጤ የሚታይባት የሃያ ስድስት ዓመት ወጣት ታካሚ ተራዋን ጠብቃ ገብታ የእርግዝና ምርመራ እንዳደርግላት ጠየቀችኝ። ምን እንደተፈጠረ ብጠይቃትም ለመናገር ፈቃደኛ አልነበረችም። እንደተባልኩት የላኩት የምርመራ ውጤት ሲመጣ እርጉዝ አለመሆኗን ያሳይ ነበር። ውጤቱን ስነግራት ግን ድንጋጤዋ ከመቀነስ ይልቅ ይበልጥ ሲጨምር አስተዋልኩ። ሊሆን እንደማይችል አስረግጣ ነገረችኝ። እንባ እየተናነቃትም “አትጠራጠር! አርግዣለሁ ዶክተር!” አለችኝ። ለምን ይህን እንደምትል ግን ለመናገር አትፈልግም። ጭራሽ ምርመራው ምንም ይበል ምን አሁኑኑ “ውርጃ” እንዲደረግላት እንደምትፈልግ ነገረችኝ።

ከብዙ ማግባባት በኋላ ግን ሁኔታውን ለማስረዳት ተገደደች። እኔ ጋር ከመምጣቷ ከስምንት ቀናት በፊት ከሁለት ወንድ የአጎቷ ልጆች እና ከታላቅ ወንድሟ ጋር የአንዱን የአጎት ልጅ ልደት ለማክበር በአንዳቸው የወንደላጤ ቤት ውስጥ “ፓሪ” ቢጤ አዘጋጅተው ሲጠጡ እና ሲጨፍሩ ማደራቸውን ነገረችኝ። ሲነጋ ግን ቀድማ እንደነቃች እና ሶስቱም ወንዶች እና ብቸኛዋ ሴት (እርሷ) አንድ ቦታ ላይ እርቃናቸውን ተኝተው እንደነበረ መመልከቷን ተናዘዘች።

በስካር ስሜት ውስጥ ሆና የፈፀመችው ለመናገር የከበዳት ነገር በከፊል ትዝ እንደሚላት፣ ነገር ግን ከአንዳቸው ይሁን ከሶስቱም ጋር ስለመሆኑ እንደማታውቅም አስረዳችኝ።

የተፈጠረው ከባድ ስህተት እንደነበረ፣ እርጉዝ ሆነችም አልሆነችም ውርጃ በዚህ ወቅት እንደማይፈፀም፣ ወዘተ… አስረድቻት፣ ከሳምንት በኋላ መጥታ የእርግዝና ምርመራውን ዳግም እንድታደርግ ስነግራት ግን ውጤቱን አሁኑኑ እንደምትፈልግ ተከራከረችኝ። ምክኒያቷ ደግሞ ይበልጥ አስገራሚ ነበር። “እጮኛ አለኝ፣ ከአንድ ሳምንት በኋላም ሠርጌ ነው” አለችኝ። ምን እንደምላት ግራ ገብቶኝ አፈጠጥኩባት… ።

👉አዘውትረው አይጠጡ ሲጠጡም መጠኖን አይለፉ የምንለው በምክንያት ነው::

Leave a Reply