October 6 2020
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያላናጋው ነገር የለም። ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉት ገደቦችም በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው፣ በሥነ ልቦና እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።
የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ አገር ሲንጋፖርም ወረርሽኙ በሌላው ዘርፍ ላይ ካሳደረው ጉዳት ባለፈ ዜጎቼ ‘ዐይናቸውን በዐይናቸው’ እንዳያዩ አድርጎብኛል ብላለች።
በወረርሽኙ ሳቢያ በገንዘብና በሥራ ማጣት ምክንያት ዜጎቿ መውለዳቸውን እየተውት አሊያም እያዘገዩት መሆኑ አሳስቧታል።
በመሆኑም እንዲወልዱ ለማበረታታት በአንድ ጊዜ የሚከፈል የገንዘብ ጉርሻ ልትሰጥ መሆኑን ገልፃለች።
የሚሰጣቸው የገንዘብ መጠን ዝርዝር ይፋ ባይደረግም፤ መንግሥት ከዚህ ቀደም ለህፃናት ከሚሰጠው ከፍተኛ ጉርሻ ጭማሪ ነው ተብሏል።
#BBC