ልጅ ሳለን ከንፈራችን ሲቆስል “ስጋ በልቼ ወይም ቅባት ያለው ምግብ በልቼ በፀሃይ ወጥቼ ነበር” ያላለ ማን አለ? ተጎ ቅጠል እና ዳማከሴ ያልተጠቀመ?
ምች (cold sore) በተለምዶ ከሚከሰቱ የቇዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛዉ ሲሆን በተለይም የላይኛዉ ወይም የታችኛዉ የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቆዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ ውሃ የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች ይታወቃል።
የምች በሽታ መምጫ ምክንያት ?
በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores ) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን ነው።
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰብ በዉስጡ ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያዎች ሲኖሩ 8ቱ በሰዉ ልጅ ላይ በሽታ ያስከትላሉ ። ከነዚህም መካከል የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 ይገኙበታል ።
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች ቆዳን ጨምሮ በኣይን፣በመራብያ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ኢንፌክሽኖች ያስከስታሉ።
የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) እንዲሁም ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2)
ከጨቅላ ህፃናት እስከ የእድሜ ባለፅጋ የእድሜ ክልል ኢንፌክሽን መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ኤች .ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) በምች አምጪ ባህሪዉ ይታወቃል። ኤች.ኤስ.ቪ -1(HSV-1) ከሰዉ ወደሰዉ በቆዳ-ቆዳ እና በቆዳ -የሚውከስ ሽፋን(የአፍ ዉስጥ ለስላሳ ሸፍን መሰል) ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2) ደግሞ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንዲሁም ከመራቢያ አካላት-ፊት በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል።
የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ዝርያዎች በነጭ የደም ሴሎቻችን ተጠግተዉ ከሰዉታችን ሙሉ በሙሉ በመወገድ ፈንታ በሰዉነታችን የነርቭ አካላት ዉስጥ በመሸሸግ የሰዉነታችን ዉስጣዊ ሁኔታዎች ምቹ እስኪሆኑ በመጠባበቅ ከተሽሽጉበት በመዉጣት በድጋሜ የምች በሽታን ያስከትላሉ ።
የምች በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?
የምች በሽታ ተህዋስያን ለመጀመርያ ጊዜ በሰዉነታችን ኢንፌክሽን ሲያስከስቱ በአብዛኛዉ ምንም ምልክት አይኖራቸዉም ነገር ግን በሚከተሉት ጊዜያት ሲከሰቱ የሚከተሉትን የመሳሰሉ ምልክቶች ልያሳዩ ይችላሉ።
የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ ፣ የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ዪችላል ከዚህም ከ24 ሰአታት በኋላ ከስራቸው ቀልተዉ ዉሃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ይፈጠራል። በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከተፈጠሩበኋላ በቀላሉ በመፈንዳት ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ዪሸፈናሉ
ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጓዳኝ የራስ ምታት ፣ ትኩሳት ፣ የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ዉስጥ የሚገጙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ እጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል። ቁስለቶቹም በተለምዶከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ።
የምች በሽታን በተደጋጋሚ የሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸዉ ?
ለሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም የመዉረድ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች (የኤች.አይ.ቪ ፣ የካንሰር ህመሞች) በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ ሆርሞናዊ ለውጦች
በተለምዶ በቫይረስ በሚመጡ እንደ ጉንፋን ባሉ ኢንፌክሽንዎች መጠቃት ጭንቀት እና የአእምሮ ዉጥረት ወዘተ
በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቤታችን ምን ማድረግ እንችላለን ?
የህመም ማስታገሻ በምች በሽታ ሚመጡ ቁስለቶች በተያያዘ የሚሰማዎትን ህመም ለመቀነስ ያለ ሃኪም ትዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን (Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን (Paracetamol) በፋርማሲ ባለሙያው ትዛዝ መሰረት መጠቀም ይቻላል ።
ቅዝቃዜ
ከምች በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን በቁስላቶቹ ዙርያ የሚከሰት የቆዳ መቅላት እና መቆጣትን ለመቀነስ በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዘያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ እንደሚረዳ የቆዳ ሃኪምዎች ዪናገራሉ።
እራስን ከጭንቀት ነጻ ማድረግ
የአእምሮ ዉጥረትን መቅነስ የሰዉነትን በሽታ መከላከል አቅም እንደሚጨምር በጥናትዎች ተረጋግጥዋል። ስለዚህም የሚያዝናኑን ነገሮችን በመፈለግ እና የአካል ብቃት አንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከዚህም በዘለለ የባለሙያ ምክር በማግኘት ልንከላከለዉ ይገባ
ለምች በሽታ የባህል ህክምናን መጠቀም ተገቢ ነዉ?
የባህል ህክምናየአንድ አካባቢ ተወላጆች ለዘመናት ያካበትዋቸዉ እንስሳን እና እጸዋት ነክ እዉቀቶችን አንዲሁም ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን መሰረት ያደረገ የህክምና ዘርፍ ነዉ። ጆርናል ኦፍ እስያ-ፓሲፊክ ባዮዲቨርሲቲ (Journal of Asia-Pacific Biodiversity) በወጣዉ ጥናት መሰረት የአለማችን 64% የሚሆነዉ ማህበረሰብ ለሚገጥሙት የጤና እክሎች የባህል ህክምናን እንደ መጀመርያ አማራጩ ይጠቀማል። በአገራችን ኢትዮጺያ ደገሞ ከ80% በላይ የሚሆነዉ ማህበረሰብ የባህል ህክምና ተጠቃሚ እንደሆነ የተለያዩ አገር በቀል ጥናቶች ያመለክታሉ።
የምእራባዉያን ባህል ህክምና በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ ፣ ብርቱካን ፣ ኪዊ እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን እንድንጠቀም ዪመክራል። የአገራችን የባህል ህክምና ደግሞ ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ሃገር በቀል ተክል ቅጠሎች ጭማቂ በመጠጣት ወይም ቅጠሎቹን አንድ ላይ በመጨፍለቅ ቁስለቶቹ ላይ በማድረግ እንድንጠቀም ይመክራል።
በዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) ጠቅላላ አጠቃቀም እንዲሁም ስለጸረ ምች አምጪ ትህዋስያን ባህሪያቱ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ስለ አጠቃላይ ጸረ-ህዋስ እና ጸረ-የሰዉነትመቆጣት (Anti-inflammatory) ባህሪያቱ የሚያወሱ አንዳንድ የሃገር በቀል ጥናቶች ብቅ ብቅ ብለዋል።
ለምች በሽታ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነዉ?