September 29 2020
የኢትዮጵያ የልብ ማእከል በየዓመቱ መስከረም19 የሚከበረው የዓለም የልብ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለ3 ቀናት የሚቆይ ነፃ የልብ ቅድመ ምርመራ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።
“የተሰበሩ ልቦችን ከልብ እንጠግን” በሚል መሪ ቃል ለሳምንት በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች የሚታሰበው የዓለም የልብ ቀን ዛሬ ተጀምሯል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከማእከሉ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
#EBC