የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የ2020 አለም አቀፍ (የፒ3) ተጽዕኖ ፈጣሪ ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

September 28 2020

የኢትዬጵያ አይን ባንክ ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት ውስጥ በብቸኝነት በሃገር ውስጥ የዓይን ብሌን በመሰብሰብ ለንቅለተከላ መአከላት በማሰራጨት ለዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

ዓይን ባንኩ እስከ ፈረንጆቹ 2019 መጨረሻ ለ2,400 ወገኖች ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸው ብርሃናቸው እንዲመለስ አድርጓል፡፡

በቨርጂኒያ ዳርደን ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ጽ/ ቤት ኮንኮርዲያ በሚያዘጋጀው አለምቀፍ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች አመታዊ ሽልማት የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የ2020 አሸናፊ በመሆን ተመርጧል፡፡

የኢትዬጵያ አይን ባንክ አሸናፊ የሆነው ከቀረቡት አምስት እጩዎች መካከል የተሻለ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ በመገኘቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የውድድሩ አሸናፊ የሆነው የኢዮጵያ የዓይን ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን በዓይን ብሌን ጠባሳ እና ተያያዥ ምክንያት የተከሰተውን ዓይነ-ስውርነት ለማጥፋት እያደረግ ባለው ከፍተኛ ጥረት እና ለማህበረሰቡ እያበረከተ ባለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሆነ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፒስሪ ኢምፓክት አዋርድ (P3 IMPACT AWARD) ተብሎ የሚጠራውን ሽልማት በማሸነፍ ሰባተኛው ተቋምም ሆኗል።

በዓለም ዙሪያ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዓይን ብሌን ጠባሳ ዓይነ ስውርነት ምክንያት በጨለማ የሚሰቃዩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከ300,000 የሚልቁት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም በመግለጫው ተነስቷል።

ፒስሪ ኢምፓክት አዋርድ (P3 IMPACT AWARD) ተብሎ የሚጠራውንና በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ጥምረት ቢሮ፣ ኮንኮርዲያ በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና በቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የሚሰጠው ይህ ሽልማት የህብረተሰቡን ችግሮች ለሚፈቱና እና ማህበረሰባዊ አገልግት ለሚሰጡ የመንግስት ፣ የግል ፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማወዳደር የሚሰጥ ሽልማት ነው።

የኢትዮጵያ የአይን ባንክ የብሌን ጠባሳ ዓይነ ስውርነት ለማስወገድ ከአጋር ድርጅቶቹ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ፣ ስይይትላይፍ እና ከሂማሊያ ካታራክት ፕሮጀክት ጋር በመሆን በአፈሪካ የልህቀት መአከል ሆኖ ለመስራት አልሞ የሚሰራ የማህበረሰብ ተቋም ነው፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap