September 28 2020
ዞስክላስ (Zosclase) ኩባንያ ከ10 ባለሀብቶች እና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኮቪድ-19 ምላሽ የሚውል 102‚500 ዶላር የሚያወጡ 1000 ታብሌት ስልኮችን በስጦታ መልክ አበርክቷል፡፡
ታብሌት ስልኮቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ትልቅ አስተዋጾ እንዳላቸው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ለድጋፉ በተዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል፡፡