You are currently viewing “በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው”፡- የዓለም ጤና ድርጅት

“በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው”፡- የዓለም ጤና ድርጅት

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 26 2020

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች አስታውቀዋል።
ባለሙያዎቹ የቫይረሱ ስርጭት የቀነሰባቸው ምክንያቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ባለሙያዎቹ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው መካከል የአህጉሪቷ ነዋሪዎች ወጣት መሆናቸው፣ ሞቃታማ የአየር ንብረት፣ ከዚህ ቀደም የዳበረ በሽታ የመከላከል አቅም መኖሩ እና በከተማ ቀመስ አካባቢዎች ጥቂት ሕዝብ መኖሩ ይጠቅሳሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እስከ 190,000 ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ብሎ መላ ምት ቢያስቀምጥም በርካታ የአፍሪካ አገሮች የወረርሽኙን ስርጭት መቆጣጠር ችለዋል።

አህጉሪቱ እንዴት በሽታውን መቆጣጠር እንደተቻለ በተደረገው የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች ውይይት ላይ እንደተገለጸው ወረርሽኙ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሳየው የተለየ ባህሪ በአፍሪካ ታይቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍረካ ኃላፊ ዶ/ር ማቲሺዲሶ ሞይቲን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት እንደተጠቀሰው ከሆነ፤ የወረርሽኙ ስርጭት ሲጀመር እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሉ ውጤት አሳይቷል።

ከሌሎች አህጉሮች አንጻር አፍሪካ ውስጥ ገደብ የተጣለው ቀድሞ ነበር። ይህም በርካታ አገሮች ላይ የምጣኔ ሀብት ጫና ማሳደሩ አልቀረም።
በአፍሪካ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ወጣቶች ናቸው። ኮሮናቫይረስ በግንባር ቀደምነት የሚያጠቃው ደግሞ አረጋውያንን ነው።
የአውሮፓ አገራትን በማነጻጸሪያነት ብንወስድ፤ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ አረጋውያን ማቆያ ውስጥ ይገባሉ።
በአፍሪካ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖራሉ። ይህ አኗኗር የበሽታውን ስርጭት ከቀነሱ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
ሌላው ምክንያት በርካታ ሰዎች በከተማ ስለሚኖሩ በሽታው ወደ ገጠር እንዳይሰራጭ መገታቱ ነው። የመሠረተ ልማት ዝርጋታው ውስን በመሆኑም ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳልተዘዋወሩ ተጠቅሷል።

ዶ/ር ማቲሺዲሶ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም እንደ ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞችን ለማስወገድ የተደረገው እንቅስቃሴ ኮቪድ-19ን በመከላከል ረገድ ጠቃሚ ሆኗል።
ሆኖም ግን ወረርሽኙ በአህጉሪቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመፈተሽ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በአፍሪካ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 34,000 ሞተዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Source :- EBC  & BBC

 

Leave a Reply