You are currently viewing 11 ክትባቶች ወደ ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ ገብተዋል‼️

11 ክትባቶች ወደ ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ ገብተዋል‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 25 2020

በአሜሪካው ጆንሰን ጆንሰን ኮርፖሬሽን የተሰራው የኮቪድ-19 ክትባት ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል:: በአሜሪካው ኖቫቫክስ የክትባት አምራች ድርጅት የተሰራው ክትባትም እንዲሁ ወደ ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ መድረሱ አጠቃላይ ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ ላይ የደረሱ የክትባቶችን ቁጥር ወደ 11 ከፍ አድርጎታል::

ሶስተኛ የሙከራ ደረጃ ላይ የደረሰ ክትባት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ ሲፈቀድለት ለሆኑ ያህል ሰዎች ክትባቱን በመስጠት ለሌሎቹ ደግሞ ሌላ የማይጎዳ ንጥረነገር በመስጠት ክትባቱ ምን ያክል ከበሽታው እንደሚከላከል ያጠናል::

የሙከራ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክትባት በጥቂት በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ ብቻ ሙከራ የሚያደርግ ይሆናል :: ይህም ክትባቱ በምን ያህል መጠን መሰጠት እንዳለበት እንዲሁም በሰዎች ላይ የቫይረሱን መከላከል አቅማቸውን በምን ያህል ማነሳሳት እንደቻለ ይጠናል:: በተጨማሪም ክትባቱ በተቀባዮቹ ላይ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ማድረስ አለማድረሱንም ይቃኛል::

ሁለተኛ የሙከራ ደረጃ ላይ የደረሰ ክትባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ሙከራ የሚያደርግ ሲሆን በዚህ ሙከራ ደረጃ ላይ ሙከራውን በህፃናት እንዲሁም በአረጋውያን ላይ ማድረግ ይችላል::

በስተመጨረሻም አራተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ክትባት ወደገበያ በስፋት ተሰራጭቶ ጥቅም ላይ እየዋለ ጎን ለጎን በሙከራ ጊዜ ያልተገኙ ጉዳቶች ወይም ጥቅሞች እንዳሉት ሪፖርቶችን በመሰብሰብ የሚታይ ይሆናል::

Leave a Reply