You are currently viewing ቫይታሚን ዲ (Vitamin D)  እና ኮቪድ-19 !!
Healthy foods containing vitamin D. Top view

ቫይታሚን ዲ (Vitamin D) እና ኮቪድ-19 !!

September 25 2020

ቫይታሚን ዲ (Vitamin D)  በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድልን በ54 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል የሰሩትን ጥናት መሰረት አርገው አንድ የቦስተን ዩኒቨርስቲ ሀኪም ተናግረዋል::

እኚህ የቦስተን ዩኒቨርስቲ ሀኪም እንደሚሉት በደም ውስጥ በቂ የቫይታሚን ዲ መጠን መኖሩ በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድልን በ54 በመቶ ሊቀንስ ይችላል::

ሰዎች ምትሀታዊ የኮሮናቫይረስ መድሀኒት ወይም ክትባት ሲጠብቁ እንደዚህ ቀላል የሆነ ነገርን አልፈለጉ አልነበረም ያሉት ዶክተር ሚካኤል ሆሊክ የተባሉ በቦስተን ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ቤት የህክምና የፊዚዮሎጂ እና የባዮ ፊዚክስ ፕሮፌሰር ናቸው::

ኩዌስት ዲያግኖስቲክስ ከተሰኘ ተቋም ያገኟቸውን ከ50ዎቹም የአሜሪካ ስቴቶች የተወጣጡ 190,000 የደም ናሙናዎችን ከስራ ባልደረባዎቻቸው ጋር በመሆን የመረመሩት ሀኪሙ በደማቸው ውስጥ አነስተኛ የቫይታሚን ዲ መጠን ያላቸው ሰዎች በቂ የቫይታሚን ዲ መጠን ካላቸው ሰዎች አንፃር በ54 በመቶ ከፍ ያለ ለቫይረሱ ፖዘቲቭ የመሆን እድል እንደሚኖራቸው አግኝተዋል::

ይህንንም አክለው ሀኪሙ የደም ውስጥ የቫይታሚን ዲ መጠን ከፍ ሲል በቫይረሱ የመያዝ እድል እንደሚወርድ ተናግረዋል::

Leave a Reply