September 20 2020
Video Description
እድሜያቸው እስከ 4 ወር የሆኑ ህፃናት ሲያለቅሱቦ ምን ያደርጋሉ ? ህፃናት በተለያዩ ምክንያቶች ሊያለቅሱ ይችላሉ:: ከእራበኝ እስከ አልተመቸኝም ከእንቅልፌ መጣ እስከ ካካ መጣብኝ አልያም ከትኩረት ስጡኝ እስከ አመመኝ ብቻ ለሁሉም ያለቅሳሉ:: አንድ የስድስት ሳምንት እድሜ ያለው ህፃን በአማካይ በቀን ውስጥ ለ3 ሰአት ከግማሽ ያክል እንደሚያለቅስ ጥናቶች ያሳያሉ::ህፃናት ለምን እንዳለቀሱ አውቆ የሚያስፈልጋቸውን ማረግ የወላጆች ሀላፊነት ነው::
ነገር ግን በጥቅሉ እድሜያቸው እስከ 4 ወር የሆኑ ህፃናት ሲያለቅሱብዎ እነዚህን 5 ኤሶች( 5 S’s) በመጠቀም እንዲረጋጉ ማድረግ አልፎም እንዲተኙ ማድረግ ይችላሉ:-
1. ልጁን በልብስ መጠቅለል( Swaddling )
2. ከዛ በጎን ወይ በሆድ እርስዎ ላይ ማስተኛት (Side/Stomach Positioning )
3. በመቀጠል ወደጆሯቸው ጠጋ ብሎ እሽ የሚል ድምፅ እያሰሙ (Shushing)
4. ሳይበዛ ቀስ ብሎ ወደዚያ ወደዚህ እያረጉ ማንቀሳቀስ (Swinging )
5. እና ፓሲፋየር በመስጠት እንዲጠቡ ማድረግ ( Sucking )
እነዚህን ስናደርግ ህፃናቱን በማህፀን ውስጥ የነበሩበትን ሁኔታ እንዲያስታውሱ በማድረግ የመረጋጋት ስሜት እንዲሰማቸው እናረጋለን::