You are currently viewing የግድያ ሙከራ በዶናልድ ትራንፕ ላይ‼️

የግድያ ሙከራ በዶናልድ ትራንፕ ላይ‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 20 2020

Castor Beans, Ricins

ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት የተላከ መርዝ አዘል ደብዳቤ ፕሬዝዳንቱ ጋር ሳይደርስ በህግ አስከባሪዎች በቁጥጥር ስር ውሏል:: ደብዳቤው ይዞት የነበረው ራይሲን ተብሎ የሚጠራ ገዳይ መርዝ እንደነበር የሁዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ለሚዲያዎች ተናግረዋል::

መርዙ የተገኘው ወደሁዋይት ሀውስ ደብዳቤ ሲላክ ምርመራ በሚደረግበት ተቋም እንደሆነ ታውቋል:: ኤፍ ቢ አይ እና የሀገሪቱ ደህንነት ደብዳቤው በማን እንደተላከ እና ከዚህ ቀደምም በዚህ መልኩ ተልከው የነበሩ መርዞች መኖር አለመኖራቸውን እየተጣሩ ይገኛሉ::

እስካሁን ለዚህ ራይሲን ተብሎ ለሚጠራው መርዝ ማርከሻ እንደሌለው ይታወቃል:: የተመረዘው ሰው ወደላይ ወደላይ ማለት ፣ ማስታወክ ፣ የውስጥ የደም መፍሰስ እንዲሁም የተለያዩ የአካል ክፍሎች ስራ ማቆም ያጋጥመዋል:: አንድ ሰው በተለያየ መልክ ለዚህ መርዝ ከተጋለጠ በኋላ ሞት ከ36 – 72 ሰአታት ባለው ይከሰታል::

#BBC

Leave a Reply