You are currently viewing አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን‼️

አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 20 2020

ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ::

ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ 400 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 4 ኪሎግራም ኮኬይን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በማይሰራ ላፕቶፕ ቦርሳ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቀጥጥር ሥር ውሏል።

ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ በላፕቶፕ ቦርሳ ለማሳለፍ የሞከረው አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በኤክስሬይ ፍተሻ አማካኝነት የተያዘ ሲሆን፤ በወንጀል ድርጊቱ ተባባሪ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሌሎች ሶሰት ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።

በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉት አራት ተጠርጣሪዎችና አደንዛዥ እፁ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀረ አደገኛ ዕፅ ዲፓርትመንት መላካቸውም ተመልክቷል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በጥናት ላይ የተደገፈ የመረጃ ስራ እያከናወነ መሆኑን በላከው መግለጫ አመልከቷል፡፡

 

#EBC

Leave a Reply