September 19 2020
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኖርዌይ የሚዘጋጀውን የ2020 የብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዘንሮውን ሽልማት በማሸነፋቸው ከአራት ቀናት በኋላ መስከረም 12 2013 ዓ.ም በኦስሎ በሚዘጋጅ ስነ-ስርዓት ይቀበላሉ ተብሏል፡፡
የአዋርዱ አሸናፊ በመሆኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ያሉት ዶክተሩ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአለምን መሰረት ነቀነቀ እንጂ መሰረቷን አልሰበራትም ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፡፡
ወረርሽኙ ለዓለም ጠንካራ ቁም ነገር አዘል ትምህርት ጥሎ ማለፉንም ጠቁመዋል፡፡
ታሪካዊውን ዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ፈተና ለመከላከል አሁንም ተባብሮ መስራትን እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ሸልማቱ የአጋርነት እና የትብብር ውጤት ማሳያ ምልክት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
For More Health related News Click Here
To Get alerts of latest News Go-to Our Telegram Channel