You are currently viewing ሩስያ የኮሮናቫይረስ ( ኮቪድ – 19) ክትባትን ልትሸጥ ነው‼️

ሩስያ የኮሮናቫይረስ ( ኮቪድ – 19) ክትባትን ልትሸጥ ነው‼️


468x60 Healthy Weight Loss Delivery Plan

September 17 2020

Doctorsonlinee.com ሩስያ የ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ክትባት ልትሸጥ ነው‼️

ክትባቱ ለማን ሊሸጥ ነው?

 

ሩስያ 100 ሚሊዮን ብልቃጥ ስፑትኒክ 5 የተሰኘውን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቷን ለህንድ ልትሸጥ ነው::

የሩስያ የኮሮና ተህዋሲያን ክትባት በህንድ ለአንድ መድኃኒት አምራች ኩባንያ ለመሸጥ ስምምነት ላይ መደረሱ ተጠቅሷል፡፡ ለክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በህንድ እንደሚካሄዱም ይጠበቃል፡፡ ሙከራዎቹ ከመድኃኒት አምራች ኩባንያው ጋር በጋራ የሚከናወኑ ይሆናል።

የሙከራውም ሆነ የአቅርቦቱ ስምምነት በህንድ የቁጥጥር ስርአት መሠረት አድርጎ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚሰጠው ፍቃድ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም የ ሩስያ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈንድ ከካዛኪስታን፣ ብራዚልና ሜክሲኮ ጋር የአቅርቦት ስምምንት ተፈራርሟል፡፡ 300 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባት ለማምረት ደግሞ የትብብር ስምምነት ከህንድ ጋር መፈራረም ተችሏል፡፡

በህንድ ክትባቱን የሚያመርተው ኩባንያ በሩሲያ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈንድ በኩል ይፋ ይሆናልም ተብሏል፡፡

የመጀመሪያው የተባለለት የ ኮሮና ቫይረሱ መከላከያ ክትባት ውጤታማ ሆኖ በዓለማችን ስሙ መዝገብ ላይ እንደሚሰፍር በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ሰፋ ያሉት ሙከራዎችም ወደ ምዕራፍ ሶስት ተሸጋግረዋል።

ሩስያ ሰራሹ ክትባት የኋሊት ታሪክ

የራሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሜር ፑቲን በነሃሴ 5 ቀን 2012 አ.ም በጠዋቱ አንዳስታወቁት ሩሲያ ሳርስ-ኮቭ 2ን ( ኮሮና ቫይረስ ) የሰው ልጅ ሰውነት አንዲቋቋመው የሚስችል ክትባት ማግኘቷንና ክትባቱ በሴት ልጃቸውም ተሞክሮ ውጤታማ አንደሆነ ተናግረው ነበር።


468x60 Healthy Weight Loss Delivery Plan

ልጃቸው ክትባቱን ከወሰደች በኋላ መጠነኛ ሙቀን እንደነበራት የገለፁቱት ፕሬዚዳንቱ ከቆይታ በኋላ ግን መጠናኛ ሙቀቱ መጥፋቱን አውስተዋል።

“እሰከማውቀው ድረስ በአለም ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ውጤታማ የሆነ ክትባት ለማስመዝገብ ችለናል። ለአለም ወሳኝ የሆነ ነገር ላበረከቱትና እዚህ ክትባት ላይ የተረባረቡ ባለሙያዎችን ሁሉ አመሰግናለው ።” በማለት ለሀገራቸው መንግስት ባለስልጣኖች ባደረጉት ንግግር ተናግረዋል።

ታዲያ ክትባቱ ይፋ በተደረገ በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ20 በላይ ሀገራት የክትባቱን 1ቢሊዮን ብልቃጥ ማዘዛቸውን ሞስኮ ተናግራ ነበር::

የኮሮናቫይረስ ክትባቱ ምርት እና ስርጭት

ከወር ገደማ በፊት ከ2 ሳምንታት በኋላ የሰራችውን የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት እንደምትጀምር ተናግራ የነበረችው ሩሲያ ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባቷን ያለችው ጊዜ ሳይደርስ በአፋጣኝ ምርቱን መጀመሯ አይረሳም::

የምርቱን ዜና ይፋ አርጎ የነበረው የ ሩሲያ ጤና ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ሲሆን ሚኒስቴሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በብዛት የሚመረተው ክትባት ባሳለፍነው ኦገስት ወር መጨረሻ ላይ መከፋፈል እንደሚጀምር ገልፆ ነበር።

የክትባት አሰጣጡን በተመለከተ የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያ ዙር የሚከተቡት የጤና ባለሙያዎችና መምህራን መሆናቸውን እና ክትባቱም ሙሉ ለሙሉ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም መናገራቸው አይረሳም።

የጤና ሚኒስትሩ የክትባት ምርት እየተከናወነ ጎን ለጎን ደግሞ ፈዋሽነቱ እየተፈተሸ ነውም ብለዋል።

የተማራማሪዎች ስጋት

አሁንም ግን በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሩሲያ በችኮላ ያመረተችው ክትባት ሌላ መዘዝ ይዞ እንዳይመጣ አሁንም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ:: በተለይም ሩስያ በአለም ዙሪያ ላሉ ተመራማሪዎች ከሳምንታት በፊት ይፋ ያደረገችውን የክትባቱን ምርምር መረጃዎች ከብዙ ተመራማሪዎች ዘንድ ትችትን ቀስቅሶባት ነበር::

ተመራማሪዎቹ ትችታቸውን የሰነዘሩት ሩሲያ ይፋ ያደረገችው የክትባቱ ምርምር መረጃ እርስ በእርሱ አይናበብም በማለት ነበር::

 

Source :-

https://www.presstv.com/Detail/2020/09/16/634224/Russia-to-sell-100mn-doses-of-COVID-19-vaccine-to-India

 


250x300 Diabetic Meals

For More Health related News Click Here

 

To Get alerts of latest News Alerts Go-to Our Telegram Channel

Leave a Reply