September 15 2020
የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ3 ወር ያህል አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት እንደጀመረ አስታውቋል።
ሆስፒታሉ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ምርመራዎችን ማካሄድና ታካሚዎችን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ወደ 25 ሺሀ የሚጠጉ ምርመራዎችን እንዳከናወነ ነው የገለፀው።
ሆስፒታሉ 270 አልጋዎችን በማዘጋጀት ከኮቪድ-19 በሽታ ጋር ተያይዞ የተለየ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች በመቀበል አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበርም ተጠቅሷል።
ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ900 ሰዎችን በመቀበል 640 ድነው መውጣታቸውና አሁን ላይ ደግሞ 150 ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቁሟል።