September 14 2020
የአለም ጤና ድርጅት ኢቦላ በኮንጎ እና በኮንጎም ውጪ ሊዛመት እንደሚችል በድጋሚ አስጠንቅቋል::
ኢቦላ በደቡባዊ ኮንጎ ግዛት እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን ይህም የቫይረሱ ስርጭት ወደአጎራባች አካባቢዎች እንዲሁም ወደኮንጎ ዋና ከተማ ኪንቻሳ ሊስፋፋ እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት ስጋቱን እየገለፀ ይገኛል::
በኮንጎ ኢኩአቲዩር ግዛት ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር መጨረሻ የተከሰተው የኢቦላ በሽታ ስርጭት አሁን በ12 ዞኖችን አጥቅቷል::
ስርጭቱ እንደአዲስ ከተቀሰቀሰ ወዲህ እስከአሁን አጠቃላይ 113 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 48 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል::
በቅርብ ጊዜ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ያስመዘገበችው ቦሞንጎ የተሰኘችው ዞን በኮንጎ ድንበር ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህም ቫይረሱ ወደአጎራባች ሀገሮች እንዳይሰራጭ ስጋት እየፈጠረ ይገኛል::
ባሳለፍነው 2012 ሚያዚያ ወር የኢቦላ በሽታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠፍቷል ብሎ ለማወጅ ሁለት ቀናት ብቻ ሲቀሩት ነበር በኢቦላ የተያዘ ሰው ተገኘ።
በጊዜው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ሚንስቴር እንዳስታወቀው በቤኒ ከተማ አንድ የ26 አመት ወጣት ነበር በኢቦላ መያዙ የተረጋገጠው።
ለ52 ቀናት በሀገሪቱ በኢቦላ የተያዘ አዲስ ሰው አለመመዝገቡን ተከትሎ ነበር ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢቦላ ነፃ ሆናለች ተብሎ ሊታወጅ የነበረው ።