You are currently viewing ፋብሪካው ተመርቋል‼️

ፋብሪካው ተመርቋል‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 13 2020

የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪቶች ማምረቻው ተመርቋል!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የመመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ::

በኢትዮጵያና በቻይና መንግስት ትብብር የተቋቋመው ፋብሪካ በዓመት 10 ሚሊየን የኮቪድ-19 ኪቶችን ያመርታል::

ቢ.ጂ.አይ ጤና ኢትዮጵያ ለሀገራችን እንዲሁም ለውጪ ሀገራት ገበያ የሚሆኑ የኮቪድ-19 ፖሊመሬስ ቼይን ሪአክሽን (ፒ.ሲ.አር) መመርመሪያ ኪቶችን ማምረት ጀምሯል። ለውጪ ሀገራት በሚደረገው ሽያጭ ለአፍሪካ ሀገራት ቅድሚያ ይሰጣል ተብሏል።
በተጨማሪም፣ ፋብሪካው ቁጥራቸው በአጠቃላይ 3 ሚሊየን ለሚደርስ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለሚያልፉ መንገደኞች በክፍያ የላብራቶሪ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ይህም የኢትዮጵያን እና የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን የመመርመር አቅም ከፍ ያደርጋል።
የኮቪድ-19 ስርጭት ከተገታ በኋላ፣ የማምረቻ ማዕከሉ የኤድስ ፣ የሳንባ ነቀርሳ እንዲሁም ሌሎች የሪል ታይም (አር.ቲ.) ፒ.ሲ.አር መመርመሪያ ኪቶችን ጨምሮ ሌሎች ኒዩክሊክ አሲድን መለያ ኬሚካሎችን ወደ ማምረት ይሸጋገራል።

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply