You are currently viewing ወደትምህርት ቤት የማይመለሱ ህፃናት‼️

ወደትምህርት ቤት የማይመለሱ ህፃናት‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 12 2020

ኮቪድ-19 ባሳደረው ተጽህኖ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ9 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ወደ ትምህርት ላይመለሱ ይችላል – ጥናት

የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ 2) ወረርሽኝ ከድሃ ቤተሰብ በተገኙ ህጻናት ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ ማድረሱን የሴቭ ዘ ችልድረን አለም አቀፍ ጥናት አሳይቷል፡፡

በሽታው በትምህርት ላይ በታሪክ ከፍተኛውን አደጋ እንደጋረጠ ነው ጥናቱ ያሳየው፡፡ በዚህም እ.ኤ.አ በ2020 9.7 ሚሊዮን ህጻናት ወደ ትምህርት የመመለስ እድል እንደሌላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በጥናቱ መሰረት ህጻናቱ በቀጣይ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለአላቻ ጋብቻና ለሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

ኮሮና ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በድሃ ቤተሰብ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ከትምህርት አለም ከማራቁ በላይ በቤት ውስጥ ለሚቃጡ ጥቃቶች ተጋለጭ አድርጓቸዋል ርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ 258 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ፕሪሚየር ታይምስ አስነብቧል፡፡

#ENA

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply