You are currently viewing ህንድ በሃገሯ የተጀመሩ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ሂደቶች እንዲቆሙ አዘዘች‼️

ህንድ በሃገሯ የተጀመሩ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ሂደቶች እንዲቆሙ አዘዘች‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 12 2020

ህንድ ሴረም የተሰኘው የክትባት መድሃኒቶች አምራች ተቋሟ የጀመረውን የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ 2) ክትባቶች የሙከራ ሂደት እንዲያቆም አዘዘች፡፡

ተቋሙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጃቸው የቫይረሱ ክትባቶች ላይ የጀመረውን የምዕራፍ 2 እና 3 ክሊኒካዊ የሙከራ ሂደት እንዲያቆምም የሃገሪቱ የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡

መድሃኒቶቹ አስትራዜናካ በተሰኘው ግዙፍ የመድሃኒት አምራች ተቋም በኩል ለሴረም ኢንስቲትዩት የደረሱ ሲሆን ተጓዳኝ የጤና እክሎችን አስከትለዋል በሚል የሙከራ ሂደታቸው ቆሟል፡፡

ይህን ታሳቢ በማድረግ በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ የክሊኒካል ሙከራ ሂደቶች እንዲቆሙ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ቀደም ሲል ለተደረጉ ሙከራዎች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥና ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

ሂደቱ ዳግም ፍቃድ እስኪያገኝ ድረስ ይቁም ያለም ሲሆን በእንግሊዝና ህንድ ከሚገኙ የመረጃ እና የደህንነት ቁጥጥር ተቋማት “ክሊራንስ” እንዲቀርብለት ጠይቋል እንደ ሂንዱስታን ታይምስ ዘገባ፡፡አስትራዜናካ የጀመረውን የሙከራ ሂደት በጊዜያዊነት እንዳቆመ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

©አል አይን

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply