You are currently viewing ሀሰተኛ ፖዘቲቭ ውጤቶች‼️

ሀሰተኛ ፖዘቲቭ ውጤቶች‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 12 2020

383 ሀሰተኛ ፖዘቲቭ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጤት የሰጠው የቦስተኑ ላቦራቶሪ ስራ እንዲያቆም ተደርጓል::

ላቦራቶሪው ስራ እንዲያቆም የተደረገው መአከሉ ሪፖርት እያረገ ያለው ከመጠን ያለፈ ፖዘቲቭ ውጤት በመንግስት አካላት እይታ ውስጥ ከገባ በኋላ ነበር::

ከስራ የማገድ ጥያቄውን ያቀረበው በአሜሪካ ማሳቹሴትስ የማህበረሰብ ጤና ክፍል ሲሆን እገዳው የተደረገው በመአከሉ የሚደረጉ የኮቪድ-19 ምርመራዎች ከሚጠበቀው ቁጥር በላይ ፖዘቲቭ ውጤት እያስገኙ ስለነበር መሆኑ ታውቋል ::

ይህ ኦሪግ 3 ኤን (Orig3n) የተሰኘው የባዮ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ወደ 60 የሚሆኑ የአልጋ ቁራኞች እና አረጋውያን መንከባከቢያ ተቋማትን ደንበኛ ያደረገ ተቋም ሲሆን መርምሮ ፖዘቲቭ ያላቸው የ383ቱ ሰዎች ምርመራ በሌላ ተቋም ተደግሞ ተሰርቶ ሰዎቹ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል::

በፈረንጆቹ ኦገስት 27 የአሜሪካው ማሳቹሴትስ የማህበረሰብ ጤና ክፍል ለድርጅቱ የ3 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶች እጥረት እንዳለበትና ይህም ህመምተኞችን አደጋ ላይ የሚጥል እንደሆነ ቢያስታውቀውም ድርጅቱ ይህንን ለማስተካል የሚረዳውን እቅድ የያዘ ሰነድ እስካሁን አላስገባም ተብሏል::

Source :-

https://www.nbcnews.com/news/us-news/coronavirus-testing-boston-lab-suspended-after-nearly-400-false-positives-n1239656

Leave a Reply