You are currently viewing ነፃ የኩላሊት እጥበት‼️

ነፃ የኩላሊት እጥበት‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 9 2020

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ::

ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡

ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት ቃል እንደገቡት በከተማዋ በመንግስት ሆስፒታሎች የሚገኙ የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሁሉም ህሙማን የአንድ አመት የህክምና ወጪያቸው በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲሰላም ከ 12 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ወደ 312 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን እና አሁን ላይ የተወሰኑት አገግመው 56 የሚሆኑ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ይህንንም ምክንያት በማድረግ በነበራቸው የምስጋና ቀን ላይ ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገው እያደረጉ ላለው ሁሉ ከልብ ምስጋና እናዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ለበዓል መዋያ 2 በሬዎችን እና 5 በጎችንም በስጦታ አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ የጤና ባለሞያዎች የሚያነሷቸውን ችግሮች በከተማ አስተዳደሩ ውይይት ተደርጎበት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

 

#EBC

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply