በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር መጨመር እንዳሳሰባት ደቡብ ሱዳን ገለፀች‼️

September 9 2020

በኢትዮጵያ በ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች።

መጋቢት ወር ላይ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ ቁጥሩ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

“በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል” በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል።

ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል።

“ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም” ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 7840 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 22 ሺህ 677 ያገገሙ ሲሆን 949 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል።

 

#BBC

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap