ኮቪድ-19 በአውሮፓ በድጋሚ እያንሰራራ መሆኑ ተገለጸ‼️

September 8 2020

ስፔን በምዕራብ አውሮፓ ግማሽ ሚሊዮን የ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች፡፡በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ525 ሺ የበለጠ ሲሆን ይህም የሆነው ትምህርት ቤቶች እንደገና ከመከፈታቸው ጋር በተያያዘ ቫይረሱ ለሁለተኛ ጊዜ በማገርሸት ላይ በመሆኑ ነው፡፡

በሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም በተመሳሳይ ቫይረሱ በድጋሚ በማንሰራራት ላይ ይገኛል፡፡ ፈረንሳይ በየቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር “አሳሳቢ” በሆነ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን ያሳወቀች ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እለት ተእለት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ ከ 5,000 በላይ መድረሱን ይፋ አድርጋለች፡፡

የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረባት ባለችው በሌላኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ዩናይትድ ኪንግደም የአገር ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ከወጣቶች የተያያዘ ስለመሆኑ ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡በመላው ዓለም እስካሁን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር ከ 27.4 ሚሊዮን በላይየደረሰ ሲሆን ከ 896,000 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፎ ከ 19 ሚሊዮን የሚበልጡት አገግመዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap