September 7 2020
ተመራማሪዎች ኮሮናቫይረስን (ሳርስ-ኮቭ2) ለመመርመር ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው መመርመሪያ መሳሪያ የሞቱ ቫይረሶችን ሲያገኝም ፖዘቲፍ ውጤት እያሳየ ሊሆን እንደሚችል አሳስበዋል::
ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ዋነኛ መመርመሪያ መሳሪያ ከዚህ በፊት ቫይረሱ ይዞት የነበረ ሰው ላይ ያሉ የሞቱ ቫይረሶችን ስብርባሪ ሲያገኝም ፖዘቲፍ ውጤት እያሳየ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል::
ብዙ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቫይረሱን ማስተላለፍ የሚችሉት ቫይረሱ ከያዛቸው በኋላ ላለ አንድ ሳምንት ገደማ ሲሆን ነገር ግን ቫይረሱን ማስተላለፍ ካቆሙ በኋላ ለሳምንታት የምርመራ ውጤታቸው ፖዘቲቭ ይሆናል::
አጥኚዎቹ እንደተናገሩት ከሆነ ይህ ሁኔታ የወረርሽኙን መጠን ከእውነተኛው መጠን ይልቅ ከፍ ብሎ እንዲገመት አርጎ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል::
የጥናቱ ፀሀፊዎች መሀል የሆኑት ፕሮፌሰር ካርል ሄኒገን እንደተናገሩት ቫይረሱን የሚመረምሩ መሳሪያዎች ቫይረሱ አለበት/ የለበትም ብሎ ከመናገር ይልቅ በሳይንስ ከተጠና ከሆነ መጠን በላይ ቫይረሱ በናሙና ውስጥ ሲገኝ ፓዘቲቭ ውጤትን እንዲሰጥ ቢደረግ እንደሚሻል ተናግረዋል::
ነገር ግን እንዲህ ያሉ ጥናቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በጥናቱ ባልተሳተፉ በቁጥር በዛ ባሉ ሌሎች ተመራማሪዎች መገምገም ይኖርባቸዋል::
[email-subscribers-form id=”1″]