“ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ” በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል : – ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ኮሚቴ

September 7 2020

በኮቪድ-19 ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት “ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል” ብለዋል።

ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል።

ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር።

ሆኖም ውድድሩን እ.ኤ.አ ከ2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል።

በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ “ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው” ብለው ነበር።

ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል።
ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር።
በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ።

“ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም” ብለዋል ሊቀመንበሩ።

የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር።

ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap