በመዲናዋ ኮቪድ-19ን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ‼️

September 7 2020

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮናቫይረስን (ኮቪድ-19ን) መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ማሻሻያውን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ ተወስኗል።

የሚኒባስ ታክሲዎች ከኋላ ባለው መቀመጫ ከ2 ሰው በላይ መጫን አይችሉም ብሏል ቢሮው በመግለጫው።

እንዲሁም ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም ነው የተገለፀው።

ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ክፍ እንዲል መደረጉንም አስታውቋል።

ከታሪፍ ጋር በተያያዘም በእጥፍ ሲከፈል የነበረው ቀርቶ መጠነኛ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ እንደሚከተለው ማስተካከያ ተደርጎበታል።

እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 1 ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን ላይ 2 ብር

ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 3 ብር የነበረው አሁን 4 ብር

ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 6 ብር

ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር በፊት 6 ብር የበረው አሁን 8 ብር

ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 10 ብር

ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር በፊት 9 ብር የነበረው አሁን 12 ብር

ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 10 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 13 ብር

ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር በፊት 12 ብር የነበረው አሁን 15 ብር

ከ20 ነጥብ 1 እስከ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 13 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 17 ብር

ከ22 ነጥብ 6 እስከ 25 ኪሎ ሜትር በፊት 15 ብር የነበረው አሁን 19 ብር

ከ25 ነጥብ 1 እስከ እስከ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 16 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 20 ብር

ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር በፊት 18 የነበረው አሁን 22 ብር ሆኖ ማሻሻያ መደረጉንም የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመግለጫው አመላክቷል።

ከተፈቀደው ሰው በላይ መጫን ከ1 ሺህ ብር ጀምሮ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 1 ሺህ 500 ብር ጀምሮ እንደሚያስቀጣም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ይህንን ለመቆጣጠር ከትራፊክ ፖሊስ በዘለለ የፖሊስና የፀጥታ አካላት መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ እና ትርፍ የሚጭኑትን ለመጠቆም የሚጠቁምበት የስክል ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይሆናል ብሏል።

 

#BBC

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap