You are currently viewing በህፃናት ላይ የሚከሰት ተቅማጥ ፣ ማስታወክ እና የሆድ ቁርጠት የኮቪድ-19 ምልክት ሊሆን ይችላል:- በኢንግሊዝ የተሰራ አንድ ጥናት

በህፃናት ላይ የሚከሰት ተቅማጥ ፣ ማስታወክ እና የሆድ ቁርጠት የኮቪድ-19 ምልክት ሊሆን ይችላል:- በኢንግሊዝ የተሰራ አንድ ጥናት

September 6 2020

በ ልጆች ላይ ጥናት ያደረገው የኢንግሊዙ ኪዊን ዩኒቨርስቲ ቤልፋስት ቡድን ሲሆን እነዚህን ምልክቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማስገባቱ ተገቢ እንደሆነ አመላክቷል::

ጥናቱ የተሰራው ወደአንድ ሺህ በሚጠጉ ህፃናት ላይ ሲሆን የህፃናቱ ደም ተወስዶ የፀረ እንግዴ (Antibody) ምርመራ ተደርጎበታል:: ይህም ልጆቹ ከዚህ በፊት ቫይረሱ ይዞ ለቋቸውም ከሆነ ለማወቅ ይረዳል::

የምርመራው ውጤት እንዳሳየው ከ992ቱ ህፃናት መሀል 68ቱ የኮሮናቫይረስ ፀረ እንግዴ (Antibody) ተገኝቶባቸዋል:: ይህም ልጆቹ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ተይዘው እንደነበር ያመለክታል::
ከነዚህ 68 ህፃናት መሀል ግማሾቹ የቫይረሱ ምልክት የነበራቸው ሲሆን ከእነዚህ መሀል 21ዱ ትኩሳት የነበራቸው ሲሆን በቁጥር በዛ ያሉ ህፃናት ሳል ነበራቸው:: 13 ልጆች ደግሞ ተቅማጥ ማስታወክ ወይም የሆድ ቁርጠት ነበራቸው::

ከልጆቹ መሀል ግን በጠና ታሞ ሆስፒታል ገብቶ የነበረ አንድም ልጅ አልነበረም::

በአሁኑ ሰአት በኢንግሊዝ እውቅና የተሰጣቸው የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት ፣ ሳል እና የማሽተት እንዲሁም መቅመስ አለመቻል ናቸው:: ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ምልክቶች መሀል አንዱም ቢሆን ካለው የቫይረሱን ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል::

ነገር ግን የአሜሪካው ሲዲሲ ተቅማጥ ማስታወክ እና ወደላይ ማለትን ከበሽታው ምልክቶች ውስጥ አስገብቷል::

#BBC

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply