You are currently viewing አፍሪካ 230 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ እንድታገኝ ማቀዱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ‼️

አፍሪካ 230 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ እንድታገኝ ማቀዱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 5 2020

የአለም ጤና ድርጅት 20 በመቶ ለሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ ወደፊት በ ምርምር ከሚገኘው የ ኮቪድ – 19 ክትባት 230 ሚሊዮን ያህል የሚሆነውን እንዲያገኝ ቅድሚያ ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል።

ክትባቱ 20 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ በይበልጥ ለጤና ባለሙያዎች እና ተጋላጭ የሆኑ አካላትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ የፕሮግራም ኃላፊ ሪቻርድ ሚሂጎ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክትባቱ ስርጭት በሀገራት የህዝብ ቁጥር አማካኝነት የሚከፋፈል እንደሚሆን ኃላፊው ገልጸዋል።

ለዚህ መሳካት የሚሰራ ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ሀገራት ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት ለማግኘት የተቋቋመ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2021 መጨረሻ ላይ ሁለት ቢሊዮን መጠን ያለው የኮቪድ ክትባት ለመግዛት እና ሁሉን አቀፍ ስርጭት እንዲኖር የሚሰራ ነው።

በሙከራ ላይ ከሚገኙት ዘጠኝ የ ኮቪድ – 19 ክትባቶች መካከል ሁለቱ በአፍሪካ ሀገራት ምርምር እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ሮይተርስ ዘግቧል።

#EBC

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply