የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የኮቪድ 19 አውቶማቲክ የናሙና መለያ እንዲሁም መመርመሪያ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

September 5 2020

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል አውቶማቲክ የ ኮሮና ቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ 2) የናሙና መለያና መመርመሪያ ማሽን በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉ ነጋ እና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ዛሬ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ቀደም ባለው ጊዜ በቫይረሱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ናሙና ወስዶ ውጤቱን ለማወቅ የሚያስችል የላብራቶሪ ምርመራ አቅርቦት በጉራጌ ዞን ያልነበረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የተጠርጣሪ ናሙና ሀዋሳ፣ አዲስ አበባ ወይም ወላይታ ሶዶ ተወስዶ ይሰራ ነበር ተብሏል። ይሄውም ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድ ተገልጾ ዩኒቨርስቲው የገዛው RT PCR ማሽን ችግሩን ይቀርፋል ሲሉ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ገልጸዋል።

ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በምረቃ ስነስርዓቱ እንደገለጹት መሳሪያው ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በሚገባ መደራጀቱን እና ማሽኑ ዩኒቨርስቲውን ከኢንስቲትዩቱ ቀጥሎ የቫይረስ ዘረመል መለያ (RNA Extractor) ያለው ብቸኛ ያደርገዋል ብለዋል።

የተደራጀው የሞሎኪውላር ላብራቶሪው በአሁኑ ጊዜ ለ ኮሮና ቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ 2)  መመርመሪያነት እንደሚያገለግልና በቀጣይ ደግሞ ለሌሎች በሽታዎች ምርመራና ለምርምር ያገለግላል ተብሏል።

ዩኒቨርስቲው ሆስፒታሉን ከተረከበበት 2008 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ለውጦች የሚያሳይ ገለጻ ለታዳሚዎች የቀረበ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ1200 በላይ የጤና ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ተብሏል።

በሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ታማሚዎችን አስተኝቶ ለማከም የሚያስችሉ 120 አልጋዎች ያሉት ማዕከል መደራጀቱንም ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ገልጸዋል።

#MoSHE

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap