September 4 2020
በ ኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የተነሳ ቢያንስ 7ሺ የጤና ባለሙያዎች ህወታቸዉን እንዳጡ አምኒስት ኢንተርናሽናል ሪፖርት አድርጓል::
አምኒስት ኢንተርናሽናል እንዳስታወቀዉ የ ኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በመላዉ ዓለም ከ7000 ያላነሱ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡
በአምኒስት ኢንተርናሽናል የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፍትህ ሀላፊ ስቴቨን ኩክበርን እንደተናገሩት ከሆነ ሁሉም የጤና ባለሙያ ደህንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑ የመረጋገጥ መብት አለዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሆኖም ይህን ባለመተግበሩ የበርካቶችን ህይወት ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል፡፡
ከተመዘገበዉ የጤና ባለሙያዎች ህልፈት መካከል በሜክሲኮ 1‚300 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡በአሜሪካ 1‚077፣በእንግሊዝ 649፣በብራዚል 634፣ በራሺያ 631 ፣በህንድ 573 የጤና ባለሙያዎች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡
በመላዉ ዓለም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 26,475,758 ሲደርስ ከነዚህ መካከል 873,289 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡በተጨማሪም በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ከተረጋገጡት መካከል ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች ስለማገገማቸዉ የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል፡፡
[email-subscribers-form id=”1″]