You are currently viewing የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤትዎ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ሊላክልዎ ነው‼️

የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤትዎ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ሊላክልዎ ነው‼️

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 3 2020

የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ያልተገኘባቸው ተመርማሪዎች ውጤታቸውን በስልካቸው የጽሁፍ መልዕክት ማድረስ ተጀመረ::

ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ላልተገኘባቸው ተመርማሪዎች በ8335 በእጅ ስልካቸው የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚያስችል ስራ ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የዲጂታላዜሺን የስራ ክፍል የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት በተቀላጠፈ መንገድ ለተመርማሪዎች ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ኤሌክትሮኒካል በማድረግ የቫይረሱን የላቦራቶሪ ውጤት በእጅ ስልካቸው እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑን ገለፀዋል።

ኢንስቲትዩቱ የላብቦራቶሪ መረጃ ስርዓቱን ከማሳደግ አንጻር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በተለይም በወረቀት ይደረግ የነበሩትን አብዛኞቹን መረጃዎች በኤሌክትሮኒክስ መለዋወጥ መጀመሩንም ጠቁሟል፡፡

የተለያዩ ስራዎች ክትትል የሚደርግባቸውን መንገድ፣ መረጃዎች የሚሰራጩባቸውን ዘዴ በየቀኑና በየሳምንቱ በወረቀት የሚላኩ ሪፖርቶች ቀርተው በኤሌክትሮኒክስ በማድረግ ስራዎችን የተቀላጠፉና በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆኑ መደረጋቸውም ተቋሙ አስታውቋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የላቦራቶሪ ናሙና የተወሰደላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ የናሙና ምርመራ ውጤት ከተረጋገጠ በኋላ ከሶስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በ8335 በመጠቀም ተመርማሪዎች ውጤቱን በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።

ውጤቱም በትክክል መድረሱን የሚያረጋግጥ የአሰራር ዘዴ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ባለሙያዎቹ ናሙና ሲወስዱ ተመርማሪዎች ትክክለኛ የስልክ ቁጥራቸውን ማስመዘገብ እንዳለባቸውም በኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የዲጂታላዜሺን የስራ ክፍል ተወካይ አቶ መስዑድ ሙሐመድ ገልጸዋል።

Source : t.me/

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply