የኬንያው አየር መንገድ ለጤና ባለሙያዎች የአውሮፕላን ቲኬት ቅናሽ ሊያደርግ ነው‼️

September 3 2020

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ወደ የትኛውም አቅጣጫ በኬንያ አየር መንገድ ሲጓዙ ግማሽ ክፍያውን አየር መንገዱ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡

በመጪው መስከረም ወር የሚጀምረው ቅናሹ ቢዝነስ ክላስና ኢኮኖሚ ከላሰን እንደሚጨመርም ተጠቅሷል፡፡

እንደ አየር መንገዱ ገለፃ በአውሮፕላን ቲኬት 50 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ የወሰነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ፊትለፊት በመጋፈጥ ህዝቦቻቸው ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ነው ብሏል፡፡

ወረርሽኝን ተከትሎ መንግስታት አየር መንገዶችን በረራ እንዲያቆሙ ከማስገደዳቸው አስቀድሞ፤ ብሔራዊው አየር መንገዱ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለመቋቋም በመስራት ላይ እንደሆም ነው የተገለፀው።

የኬንያ የፓርላማ አባላት ያለፈው ሐምሌ ወር አየር መንገዱን ከኪሳራ ለመታደግ ድጋፍ ማድረግ እንደሚስፈልግ ድምጽ መስጠታቸውን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#ENA

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap