“ሙሰኛ በሆኑት የአለም ጤና ድርጅት እና ቻይና በሚመሩ ትብብሮች አሜሪካ አትገደብም”- የሁዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጁድ ድሪ

September 2 2020

አሜሪካ በአለም ጤና ድርጅት በሚመራው አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ክትባት የማግኘት ጥረት አካል አልሆንም ብላለች::

ባሳለፍነው ማክሰኞ ሀገሪቷ በአለም የጤና ድርጅት በሚመራው አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ክትባት የማግኘት እና የማሰራጨት ጥረት አካል አልሆንም ብላለች::

ይህም የሆነው የትራንፕ አስተዳደር ለኮቪድ-19 ምላሽ የሚሰጠው አለም አቀፍ ማህበረሰብ መሪ የሆነው የአለም ጤና ድርጅት በመሆኑ እንደሆነ አረጋግጧል::

በአለም የጤና ድርጅት በሲኢፒአይ እና በጋቪ የሚመራ ኮቫክስ(Covax) የተሰኘ ትብብር አለ:: ትብብሩ ክትባቱን ካገኙ ድርጅቶች በ2021 መጨረሻ ላይ አጠቃላይ 2 ቢሊዮን የሚያህሉ ክትባቶችን ለመግዛት እና ለማሰራጨት ያለመ ነው::

የአለም ጤና ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ እንዳረገው ኮቫክስ ክትባቶቹ ላይሰንስ ካገኙ እና ከፀደቁ በኋላ የኮቫክስ ትብብር ላይ ተሳታፊ ለሆኑ 172 ሀገራት ደህንነታቸው የተጠበቁ ፍቱን ክትባቶችን ለማሰራጨት አልሟል::

የአውሮፓ ኮሚሽን በበኩሉ ለዚህ ትብብር የሚውል 428 ሚሊዮን ዩሮ እንደመደበ ባሳለፍነው ሰኞ ይፋ አርጓል::

የሁዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጁድ ድሪ ግን እንደተናገሩት አሜሪካ ወረርሺኙን ለመግታት ከአለም አቀፍ ተባባሪዎቻችን ጋር መስራት ትቀጥላለች ነገር ግን አሜሪካ ሙሰኛ በሆኑት አለም የጤና ድርጅት እና ቻይና ተፅእኖ ስር ባሉ ድርጅቶች አትገደብም ብለዋል::

 

#Forbes

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap