ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ በሚከሰት ረሃብ በየቀኑ 426 ህፃናት የመሞት አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡- የህፃናት አድን ድርጅት

September 1 2020

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በሚከሰት ረሃብ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በየቀኑ 426 ህፃናት የመሞት አደጋ አንደተጋረጠባቸው የህፃናት አድን ድርጅት አስታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ 2020 ከመጠናቀቁ በፊት 67 ሺህ ገደማ ህፃናት የመሞት ስጋት ተደቅኖባቸዋል ብሏል ድርጅቱ፡፡

የኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) ስርጭትን ለመቆጣጠር አስቸኳይ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በየቀኑ 426 ህፃናት ህይወት ልያልፍ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በቀጠናው በተከሰተው ጎርፍና የአንበጣ መንጋ ከቀያቸው በተፈናቀሉ አካላት ላይ ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ጭማሪ እንዲከሰትም አድርጓል ተብሏል፡፡

ወረርሽኙ በደቀነው ችግር ምንያት በርካቶች ከስራ ገበታቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡ ችግሩን ለመቀነስ ድርጅቱ እያደረገ ላለው ጥረት ለማገዝም የተለያዩ ለጋሽ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ነው ጥሪ መቅረቡን የሪሊፍዌብ ዘገባ ያመለክታል፡፡

 

#EBC

 

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap