You are currently viewing ሩስያ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ልታሰራጭ መሆኑን አስታወቀች።

ሩስያ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ልታሰራጭ መሆኑን አስታወቀች።

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments

September 1 2020

ሩስያ ከ25 ሚሊየን በላይ የዓለም ህዝብ ላጠቃው የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ክትባትን ማምረት ጀምራለሁ ካለችበት ጊዜ በሳምንታት ቀደማ ማምረት መጀመሯ ይታወሳል። የክትባት አሰጣጡን በተመለከተ የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያ ዙር የሚከተቡት የጤና ባለሙያዎችና መምህራን መሆናቸውን እና ክትባቱም ሙሉ ለሙሉ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም መናገራቸው አይረሳም።

የጤና ሚኒስትሩ የክትባት ምርት እየተከናወነ ጎን ለጎን ደግሞ ፈዋሽነቱ እየተፈተሸ ነው ብለዋል።

እስከ አሁን ለሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ከተመዘገቡ 40 ሺህ በጎ ፈቃደኞች መካከል 2 ሺህ 500 ሰዎች መመረጣቸውንም አስታውቀዋል።
በአንጻሩ ምዕራባውያን የክትባቱ ፈዋሽነት ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፦ ሩስያ በበኩሏ ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋለች። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የሩሲያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለመመዘንም ከሀገሪቱ በቂ መረጃ እንዳላገኘም እየተነገረ ይገኛል።

ምንጭ : ዋልታ

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply