August 31 2020
በኢትዮጵያ ከተከሰተ ስድስት ወራት ሊደፍን የተቃረበው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የ ሙዚቃ ባለሙያዎች ኑሮ ላይ ጫናው በመበርታቱን የ ሙዚቃ ዘርፍ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት ዳዊት ይፍሩ ገልጸዋል።
የኮሮናቫይረስ መከሰት በተለይ በሆቴሎች እና ምሽት ክለቦች ይዘጋጁ የነበሩ የሙዚቃ መድረኮች ያለመኖራቸው የበርካቶችን የዕለት ጉርስ ነፍጓልም ብለዋል።
ማኅበሩ የተወሰኑትን አርቲስቶች ችግር በጊዜያዊነት ሊፈታ ይችላል ያለውን መላ ዘይዶ መንቀሳቀሱንም አስረድተዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ስፖንሰር በማፈላለግ “ተመልካች አልባ” ኮንሰርት በማዘጋጀት ከ100 በላይ ሙያተኞችን ማገዝ እንደተቻለም አስታውሰዋል።
በመንግሥት ድጋፍ ብቻ ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ የማይችል በመሆኑ እንደ ተዘዋዋሪ ፈንድ ድጎማ ለማግኘት የሚያስችል ተስፋ መሰነቁን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
በቀጣይም ከሚዲያ ተቋማት ጋር በመተባበር ሥራዎችን ለኅብረተሰቡ በማቅረብ ችግር ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ለመታደግ ጥረት እንደሚደረግ እና ለዚህም ከስፖንሰር አድራጊዎች ፈቃደኝነት መገኘቱን ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙኃን እና ኪነ-ጥበብ ተነጣጥለው መጓዝ እንደማይችሉ የገለጹት አርቲስት ዳዊት ይፍሩ፣ ይህን መጥፎ ጊዜ ለማለፍ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#EBC
[email-subscribers-form id=”1″]