የኮሮናቫይረስ(ኮቪድ-19) ስርጭት ሊያባብስ የሚችል የስራ ባህሪ ያላቸው ድርጅቶች ዘርፍ ለመቀየር ከፈለጉ በአፋጣኝ ይስተናገዳሉ – የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

August 31 2020

የኮቪድ-19 ስርጭት ሊያባብስ የሚችል የስራ ባህሪ ያላቸውና ዘርፍ ቀይረው ለመስራት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች ቀልጣፋ መስተንግዶ እንደሚደረግላቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ በሽታውን የመከላከልና ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተነስቷል፡፡

ዜጎችን ከበሽታው ለመከላከል ሲባል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተዘረዘሩና መዘጋት ያለባቸው ድርጅቶች የመዝጋት እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ ዩሱፍ አስታውሰዋል፡፡

ድርጅቶቹ እንዲዘጉ የተደረገበት ዋና አላማ የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ነው፡፡

በመሆኑ አጋላጭ ወዳልሆኑት የስራ ዘርፎች ለመቀየር ለሚፈልጉ የንግዱ ማህበረሰብ በራችን ክፍት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለበሽታ መስፋፋት መናሃርያ የሆኑና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተዘረዘሩት ተቋማት ግን የቫይረሱ ስርጭት ቀንሶ በአገራዊ ኮቪድ-19 የሚኒስትሮች ኮሚቴ አምኖበት እስኪያነሳ ድረስ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አብራርተዋል፡፡

 

#EBC

 

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap