August 30 2020
#Elon_Musk
👉 በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆነው አሜሪካዊ ቢሊየነር ኢለን መስክ አንድ በአይነቱ የተለየ የፈጠራ ውጤትን ለህዝብ አቅርቧል:: ስራ ፈጣሪው (Entrepreneur) ኢለን መስክ በፈረንጆቹ 2016 የመሰረተውን ኒውራ ሊንክ የተሰኘ የሰውን አእምሮ ከማሽን ጋር በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ ኩባንያ አንድ የስራ ውጤትን በዚህ ሳምንት ይፋ አድርጓል::
👉 ኢለን መስክ አንድ ገርትሩድ የተሰኘ አሳማ ጭንቅላት ውስጥ ኒውራ ሊንክ በቀበረው ሳንቲም የሚያክል መሳሪያ በመታገዝ አሳማዋ የምታሸተውን ነገሮች በሲግናል መልክ ወደ ኮምፒተር አስተላልፎ ለእይታ አብቅቷል:: እንደ ኢለን መስክ ከሆነ አሳማዋ መሳሪያው ከተቀበረላት 2 ወር ቢሆነውም እስከአሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች::
👉 ቢሊየነሩ ወደፊት እንዲህ አይነት መሳሪያ በሰው ጭንቅላት ውስጥ በመግጠም በተለያየ ምክንያት ሽባ የሆኑ ሰዎች በቀላሉ ስልክ እንዲጠቀሙ ወዘተ … ማድረግ እንደሚቻል ተናግሯል:: መሳሪያው የሚገጠመው ሙሉ በሙሉ በሮቦት ሲሆን አንድ ሰው መሳሪያው ከገባለት በኋላ በፈለገው ጊዜ እንዲወጣለት ማድረግ እንደሚችልም ተናግሯል::
👉👉ነገር ግን ይህ ፕሮጀክት ከብዙ ወገኖች ትችት እያስነሳበት ይገኛል::