You are currently viewing የማህፀን በር ካንሰርን መከላከል ይቻላል‼️ August  2020

የማህፀን በር ካንሰርን መከላከል ይቻላል‼️ August 2020

468x60 Healthy Weight Loss Delivery Plan
August 30 2020

የማህፀን-በር-ካንሰርን-መከላከል-ይቻላል

የማህፀን በር ካንሰር ምንድነው?

 

የማህፀን በር ካንሰር ማለት ወደ ማህፀን መግቢያ በር ( የ ማህፀን የታችኛው ክፍል) ላይ የሚፈጠር ካንሰር ነው።ይህም የሚሆነው በማህፀን የታችኛው ክፍል የሚገኙ መደበኛ ቁጥር ያላቸው ሴሎች መደበኛ ያልሆነ ቁጥር ባላቸው ሴሎች ሲተኩ እና ከሰውነታችን የሴል መራባት ቁጥጥር ውጪ ራሳቸውን በሚያራቡበት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ መደበኛ ያልሆኑ ሴሎች ከመራባት አልፈው ከአካባቢያቸው ራቅ ወዳለ የሰውነታችን ክፍል የሚዛመቱበት ሁኔታ በቀላሉ ይፈጥራሉ፡፡

የማህፀን በር ካንሰር ምን ያህል የተለመደ ነው?

ከሌሎች የካንሰር አይነቶች አንፃር የማህፀን በር ካንሰር በአለም ላይ ብዙ ሴቶችን በማጥቃት ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ እያደጉ ባሉ ሀገራት የሴቶችን ህይወት በመቅጠፍ ቀዳሚ የካንሰር አይነት ነው። ይህ በሽታ ባሳለፍነው በ2019 ብቻ በዩናይትድ ስቴትስ ከ 17,170 በላይ ሴቶችን አጥቅቷል።

እኛም ስለዚህ የካንሰር አይነት ማብራራት የፈለግንበት ዋነኛ ምክንያት በሀገራችን ካንሰሩ የበርካታ ሴቶችን ውድ ህይወት እየቀጠፈ ስላለና ካንሰሩን መከላከል የሚያስችሉ ክትባትን ጨምሮ የተለያዩ መንገዶች ስላሉ ነው ።

468x60 Healthy Weight Loss Delivery Plan

የ ማህፀን በር ካንሰር ሲነሳ መነሳቱ የማይቀር አንድ ቫይረስ አለ:: ይህም ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(Human Papiloma Virus) ይባላል ። ይህ ቫይረስ ለካሰሩ መከሰት ዋናውና ቀዳሚው ምክንያት ነው። ስለዚህም የዚህን ቫይረስ ክትባት መውሰድ እና በየጊዜው አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የ ማህፀን በር ካንሰርን መከላከል ይቻላል። ካንሰሩ ከተከሰተ በኋላም እንደየደረጃው ህክምና አለው::

ለማህፀን ጫፍ ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ሁኔታዎች መካከል ዋናዎቹን እነሆ

1. ከአንድ በላይ የፍቅር አጋር ያላቸው ሴቶች፡፡ አንዲት ሴት የሚኖራት የፍቅር አጋር ቁጥር ሲጨምር በሽታውን ሊያመጡ ለሚችሉ ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(Human Papiloma Virus) አይነቶች ያላት ተጋላጭነት ይጨምራል::
2. አንዲት ሴት ያላት የትዳር አጋር አንድ ቢሆንም አጋሯ ከአንድ በላይ የፍቅር አጋር ያለው ከሆነ እና በተጨማሪም በሂዩማንፓፒሎማ ቫይረስ የተጠቃ ከሆነ የመጋለጥ ሁኔታቸው ከፍተኛ ነው፡፡
3. ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች የተጠቁ ሴቶች የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም እንዲቀንስ የሚያደርጉ ኤች አይቪ መሰል የጤና ችግር ያለባቸውም ሴቶች በይበልጥ ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ይጋለጣሉ፡፡
4. ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች ሆነው ግንኙነት የሚጀምሩ ሴቶች ለበሽታው ተጋላጪነታቸው ይጨምራል::
5. ሲጋራ ማጨስ.
6. ለረጅም ጊዜ በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መቆጣጣጠሪያዎችን መጠቀም
7. 3 እና ከዛ በላይ ልጆችን መውለድ

የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምልክቶች

ብዙን ጊዜ ሕመሙ ምልክት ሳይሰጥ ለበርካታ አመታት ሞቆየት ይችላል፡፡ የመጀመሪያ አካባቢ ብዙውን ጊዜ ምልክት አያሳይም። አልፎ አልፎ የዳሌ አጥንት ዙሪያ ያልተለመደ ስሜት ከመፍጠር ውጪ። በዚህ ጊዜ ወደ ጤና ተቆም መሄድና ምርመራ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ መከላከያ መንገድ ነው።

250x300 Diabetic Meals

ይሁንና የካንሰር ደረጃ ከደረሰ ቀጥሎ ያሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡

1. በግንኙነት ወይም በሚታጠቡበት ጊዜ ከወር አበባ ጋር ባልተገናኘ መልኩ የደም መፍሰስ

2. አልያም መጠኑ የበዛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ

3. የማህፀን ሕመም
4. የወገብ ሕመም
5. የሽንት ፊኛ የመቆጣጠር ችግር
6. አይነምድር የመቆጣጠር ችግር
7. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
8. የሰውነት መድከም የመሳሰሉት ናቸው፡

የማህፀን ጫፍ ካንሰር እንዴት እንከላከል

1. ራስን ከአባላዘር በሽታዎች መከላከል

2. አንድ ለአንድ በመፅናት እና ጊዜውን ካልጠበቀ የግበረ ስጋ ግንኙነት ራስን ማቀብ

3. ቋሚ የሆነ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ

? የቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማለት አንድ ህመሙ ተከስቶ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በማወቅ አስፈላጊውን ህክምና ወይንም ጥንቃቄ ማድረግ ማለት ነው፡፡

? ምርመራው በተለይ ለማን የስፈልጋል?

I. እድሜዋ ከ21 ዓመት በላይ የሆነና ወንድ የምታውቅ

II. ከዚህ በፊት ተመረምራ ነፃ ከተባለች 3 ዓመት ያለፋት

III. የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የምትወስድ ወይም የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ በደሟ ውስጥ ያለ።

? ምርመራ ምን ይጠቅማል?

A. ካንሰር አለመኖሩን ማረጋገጥ

B. የቅድመ ካንሰር ምልክቶች ካሉ ባግባቡ ለመታከም

C. የተረጋገጠ ካንሰር ከተገኘ በወቅቱ ህክምናውን በመውሰድ ለመዳን

D. ውጤትን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ።

? በሀገራችን ውስጥ በየዓመቱ ሆስፒታል ለህክምና መጥተው ሲመረመሩ ከ7000 በላይ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካን ሰር ተጋልጠው ተገኝተዋል፡፡ ከነኚሁ ውስጥ ከ6000 በላይ የሚሆኑት በዛው ዓመት ይሞታሉ። ይህ ስሌት የሚያመለክተው ህመም ኖሯቸው ለመታከም ወደ ህክምና ማእከል የመጡትን ሴቶች ብቻ ነው።

4. የካንሰሩን መከላከያ ክትባት መውሰድ
5. ሲጃራ ማጨስ ማቆም

ለማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚሰጡ ሕክምናዎች

1. ሕክምናው እንደ ደረጃው ይለያያል:: የ ማህፀን በር ካንሰር አራት ደረጃዎች ሲኖሩት የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን በአፍ በሚወሰድ ክኒን፡ በጨረር፡ በቀዶ ህክምና ወይም ከሶስቱ በሁለቱ ሙሉ ለሙሉ አክሞ ማዳን ይቻላል።
2. በሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰን የካንሰር አይነትን ሙሉ ለሙሉ አክሞ ማዳን ቢያስቸግርም የዘርፉ ሀኪሞች በሚያዟቸው የህክምና አይነቶች ማድረግ በህይወት የመቆየት እድልን ከፍ ማድረግ ይቻላል:: አራተኛ የካንሰር ደረጃ ላይ ከደረሰ ካንሰርን ማከም እጅግ አስቸጋሪ ነው::

ስለዚህ ሴቶች ይህን በሽታ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አስቀድሞ በመመርመር እና ክትባቱን በመውሰድ በሚገባ መከላከል እንደሚችሉ ልናሳስብ እንወዳለን::

ይህን ፅሁፍ ሼር በማድረግ የ ማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል የበኩሎትን ያድርጉ::

Source :-

World Health Organization 

Medscape

If you Want to Read Other Articles on Health care Education Click Here


[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply